Skip to main content
x

የዲፕሎማቶቻችን ሹመት በብቃት ላይ ብቻ የተመሠረተ ይሁን

የመንግሥት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በተደጋጋሚ አንስተን ጥለናል፡፡ እከሌ ከእከሌ ሳይባል ለሕዝብ አገልግሎት የተቋቋሙ መሥሪያ ቤቶች ብዙዎችን አሰነብተዋል፡፡ አማረዋል፡፡ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ‹‹የመንግሥት ያለህ›› ያስባሉ የመንግሥት ተቋማት ‹‹በሽ›› ናቸው፡፡

አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፍሪካ ኅብረት አቀረቡ

በቅርቡ በአፍሪካ ኅብረትና በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር አቀረቡ። በባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ዘርፍ የረጅም ዓመታት ልምድ ያካበቱት አምባሳደር ወይንሸት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኅብረቱ ኮሚሽን ሙሳ ፋኪ ማሃመት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ማቅረባቸውን፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

‹‹ኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ጫናውን ለብቻቸው ስለተሸከሙ ዕዳ አለብን››

የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን በመገንባት ጫናውን ለብቻቸው እንደተሸከሙ፣ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር ተናገሩ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን መልዕክት ሲያደርስና በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በተነጋገረበት ወቅት መሆኑን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹የግብፅን የዓባይ የውኃ ድርሻ ማንም እንደማይነካው ለግብፃዊያን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ›› አብዱልፈታህ አልሲሲ፣ የግብፅ ፕሬዚዳንት

በህዳሴ ግድቡ ላይ ስምምነት መፍጠር እንዳልተቻለ ግብፅ ለአሜሪካ ማሳወቋ ተጠቁሟል የግብፅን የዓባይ የውኃ ‹‹ለአገሪቱ የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው›› ያሉት የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ በመካከለኛው ምሥራቅ ትልቁ ነው የተባለው የዓሳ ማምረቻ ከቀናት በፊት በተመረቀበትና በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው፣ ‹‹የግብፅን የዓባይ የውኃ ድርሻ ማንም እንደማይነካው ለግብፃዊያን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፤›› ብለዋል፡፡

ከውጭ የሚመጡ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ተከታትሎ ለውጤት የማድረስ ችግሮች እንዳሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ

በተለያዩ የንግድና የኢንቨስትመንት ፎረሞች ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የንግድ ልዑካንን ተከታትሎ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉ ላይ ክፍተት እንደሚታይ ተገለጸ፡፡ በአገሪቱ የሚካሄዱ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት ምክክር መድረኮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ ቢመጣም፣ ፍሬያማነታቸውን እስከ መጨረሻው በመከታተል ለውጤት ማብቃቱ ላይ ብዙ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተጠቅሷል፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ 34 የቢዝነስ ፎረሞች ተካሒደዋል፡፡

ለአሜሪካ የኮንግረስ አባላት የቀረበውን የሰብዓዊ መብት የውሳኔ ሐሳብ መንግሥት አጣጣለው

የአሜሪካ ኮንግረንስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምፅ እንዲሰጥበት፣ በአሜሪካ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ያቀረቡትን ጥያቄ መንግሥት አጣጣለው፡፡

የህዳሴ ግድቡን ተፅዕኖና የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅ የሚያጠናው ድርጅት መመርያ ተዘጋጀለት

የህዳሴ ግድቡ በታችኞቹ የተፋሰስ አገሮች ላይ ሊኖረው ስለሚችለው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ተፅዕኖ፣ የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅ ለማስጠናት በድርድር ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ፣ በአዲስ አበባ ለ16ኛ ጊዜ ተገናኝተው ጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. መከሩ፡፡ የጥናቱ አማካሪ ድርጅት አሠራሩን የሚመራ ረቂቅ መመርያ ላይ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

‹‹በኢትዮጵያ ለሚታየው የፖለቲካ ውጥረት አስፈላጊውን መፍትሔ ለማምጣት እንተባበራለን››

የአሜሪካ ሴናተር ጀምስ ኢንሆፍ በኢትዮጵያ የሚታየውን የፖለቲካ ውጥረት ለመቅረፍ አስፈላጊ የሚሆነውን መፍትሔ ለማምጣት እንደሚረባረቡ፣ በአሜሪካ ሴኔት ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሴናተር ጄምስ ኢንሆፍ አስታወቁ፡፡

የኢጋድ አባል አገሮች የደቡብ ሱዳን ተገዳዳሪ ኃይሎችን ለማስታረቅ እየጣሩ ነው

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና ዋነኛ ተቃዋሚያቸው ሪክ ማቻር (ዶ/ር) መካከል ያለውንና ጉዳት እያስከተለ ያለውን ልዩነት ለመፍታት፣ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዓርብ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በጁባ ውይይት አደረጉ፡፡