Skip to main content
x

የነዳጅ ኩባንያዎች ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ መግባታቸውን አስታወቁ

በነዳጅ ማከፋፈል ሥራ የተሰማሩ ኩባንያዎች ለሚሰጡት አገልግሎት የሚከፈላቸው የትርፍ ህዳግ በጣም አነስተኛ መሆን፣ ለዘርፉ መቀጨጭ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስታወቁ፡፡ ቅዳሜ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢሊሊ ሆቴል የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመገምገም ባሰናዳው የምክክር መድረክ ላይ፣ የነዳጅ ኩባንያዎች ኃላፊዎች በተለያዩ ጊዜያት መንግሥት ለነዳጅ ኩባንያዎች የፈቀደው የትርፍ ህዳግ በጣም አነስተኛ መሆኑን በመግለጽ እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ዕርምጃ ባለመወሰዱ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለውን የባቡር መስመር በዲዝል ኃይል የትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር መታቀዱ ተሰማ

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው የባቡር መስመር ከሞላ ጎደል እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣ በዲዝል ኃይል የትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር ማቀዱን ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች አመለከቱ።

ጎርባጣው ባቡር

በጉጉት ሲጠበቅ በነበረው የአዲስ ጂቡቲ የምድር ባቡር መሳፈር ጀምረናል፡፡ ከአዲስ አበባ ጅቡቲ ድረስ በሚዘልቀው የባቡር መስመር ወደ 19 ከተሞች መጓዝ ቢቻልም፣ በአሁኑ ወቅት መንገደኞች የሚያስተናገዱት በአራት ከተሞች ብቻ ነው፡፡ አዲሱ የኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር በቅርቡ ጉዞ የጀመረው 28 ተሳፋሪዎችን ይዞ ነበር፡፡ ከዚያን ወዲህ ያለው የተሳፋሪ ቁጥር ከዚህ በላይ እንደጨመረ ይታመናል፡፡ ብዙ የሚጠበቅበት የመንገደኞች የባቡር ትራንስፖርት አጀማመሩ ስንጠብቀው የነበረውን ያህል አልሆነም፡፡ የባቡሩ ጉዞም ቢሆን ከትክክለኛው የፍጥነት ወሰን በግማሽ ቀንሶ የሚጓዝ ነው፡፡ በአራት ሰዓት ‹‹ድሬ›› የመድረስ ጉልበት ያለው ፈጣኑ ባቡራችን፣ አሁን ላይ ድሬ ለመድረስ ሰባት ሰዓታት ይወሰድበታል፡፡

ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርን ሙሉ ለሙሉ ተረክቦ ማስተዳደር ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲያስተዳድረው ከነበረው የቻይና ኩባንያ ተረክቦ፣ በራሱ ማስተዳደር ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር ማሠልጠኛ ሊገነባ ነው

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከቻይና መንግሥት ባገኘው የገንዘብ እርዳታ በቢሾፍቱ ከተማ በ151.7 ሔክታር መሬት ላይ የባቡር አካዳሚ ለመገንባት ከቻይና ኤምባሲ ተወካዮች ጋር ዛሬ ጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. የእርዳታ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

 

የቻይና መንግሥት ለፕሮጀክቱ 373.15 ሚሊዮን ዩዋን (1.57 ቢሊዮን ብር) እርዳታ የሚሰጥ ሲሆን፣ ግንባታው በመስከረም 2011 ዓ.ም. እንደሚጀመር ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የግንባታ ቦታ የማዘጋጀትና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችም እየተጠናቀቁ እንደሆነ ታውቋል፡፡

 

ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ግዙፍ ወጪ የነዳጅ ማከማቻ ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ ነው

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል የተባለ ግዙፍ አዲስ ዘመናዊ የነዳጅ ማከማቻ በዱከም ከተማ ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡ በአዋሽ ሰባት ያስገነባው የነዳጅ ማከማቻ ቢጠናቀቅም፣ አገልግሎቱን ለመጀመር የባቡር መስመር ዝርጋታ እየተጠበቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከጂቡቲ ኢትዮጵያ ሊዘረጋ የታሰበው የነዳጅ መስመር ፕሮጀክት ታጠፈ

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ ከጂቡቲ ወደብ ወደ መሀል አገር የምታስገባው የተጣራ የነዳጅ ውጤቶች ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክት እንደታጠፈ ታወቀ፡፡ ተቀማጭነቱ በደቡብ አፍሪካ የሆነው ብላክ ራይኖ የተባለ ኩባንያ ከጂቡቲ ወደብ አዋሽ አርባ የሚገኘው የነዳጅ ዴፖ የሚደርስ 550 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ለመዘርጋት የሚያስችል ዕቅድ፣ ለኢትዮጵያ መንግሥት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ዘንድሮ የአዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ አይኖርም

ኢትዮጵያ ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ ከአዋሽ-ወልዲያ-መቀሌ የባቡር መስመር ዝርጋታ እያካሄደች ቢሆንም፣ ዘንድሮ አዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ እንደማይጀመር ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ አገሪቱ ሁለት የባቡር መስመር ፕሮጀክቶችን እያከናወነች ቢሆንም ዘንድሮ የሚጀመር ፕሮጀክት የለም፡፡ ከመቼ ጀምሮ የአዳዲስ የባቡር መስመሮች ዝርጋታ እንደሚጀመር አይታወቅም ብለዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር መስመር 106 ኮንቴይነሮችን በማጓጓዝ የሙከራ የትራንስፖርት አገልግሎት ጀመረ

የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቶችን እያጠናቀቀ የሚገኘው አዲሱ የአዲስ አበባ ጂቡቲ ምድር ባቡር መስመር 106 ኮንቴይነሮችን በአንድ ጊዜ ከጂቡቲ ወደብ በመጫን የሙከራ የትራንስፖርት አገልግሎት ጀመረ፡፡