Skip to main content
x

የ70 ዓመታት የነዳጅ ፍለጋ ጥረት ፍሬ እያፈራ ነው

ላለፉት 70 ዓመታት በኦጋዴን ቤዚን ሲካሄድ የቆየው የነዳጅ ፍለጋ ሥራ ፍሬ እያፈራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ ፖሊጂሲኤል ፔትሮሊየም ኢንቨስትመንት የተባለው የቻይና ሂላላ በተባለው ሥፍራ ያገኘውን የተፈጥሮ ዘይት ሐሙስ ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. የሙከራ ምርት ማውጣት ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትና ስሜክ በዱከም የሚገነባውን የነዳጅ ዲፖ ዲዛይን ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በዱከም ከተማ አቅራቢያ በከፍተኛ ወጪ ለመገንባት ያቀደውን ግዙፍ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዲፖ የዲዛይንና ፕሮጀክት ክትትል ሥራ ውል ስሜክ ኢንተርናሽናል ከተባለ የአውስትራሊያ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ፡፡

የነዳጅ ኩባንያዎች ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ መግባታቸውን አስታወቁ

በነዳጅ ማከፋፈል ሥራ የተሰማሩ ኩባንያዎች ለሚሰጡት አገልግሎት የሚከፈላቸው የትርፍ ህዳግ በጣም አነስተኛ መሆን፣ ለዘርፉ መቀጨጭ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስታወቁ፡፡ ቅዳሜ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢሊሊ ሆቴል የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመገምገም ባሰናዳው የምክክር መድረክ ላይ፣ የነዳጅ ኩባንያዎች ኃላፊዎች በተለያዩ ጊዜያት መንግሥት ለነዳጅ ኩባንያዎች የፈቀደው የትርፍ ህዳግ በጣም አነስተኛ መሆኑን በመግለጽ እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ዕርምጃ ባለመወሰዱ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመንግሥትና በነዳጅ አቅራቢዎች መካከል አዲስ አለመግባባት ተፈጠረ

አራቱ ትልልቅ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ኖክ፣ የተባበሩት፣ ቶታልና ኦይል ሊቢያ የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ያቀረበላቸውን አዲስ ውል አንቀበልም ማለታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ በመንግሥታዊ ነዳጅ ድርጅትና በግል ነዳጅ አቅራቢዎች መካከል አዲስ አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡

አሽከርካሪዎች ሥጋት ስለገባቸው ኮማንድ ፖስቱ ነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን አጀበ

ከማክሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከጉዞአቸው እንዲስተጓጎሉ ጥሪ ተላልፏል ተብሎ በማኅበራዊ ሚዲያ በተናፈሰው ወሬ ጭንቀት የገባቸው አሽከርካሪዎች በመኖራቸው፣ በኮማንድ ፖስት የሚመራው የፀጥታ ኃይል ተሽከርካሪዎችን በማጀብ ወደ አዲስ አበባ ሸኝቷል፡፡

ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ግዙፍ ወጪ የነዳጅ ማከማቻ ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ ነው

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል የተባለ ግዙፍ አዲስ ዘመናዊ የነዳጅ ማከማቻ በዱከም ከተማ ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡ በአዋሽ ሰባት ያስገነባው የነዳጅ ማከማቻ ቢጠናቀቅም፣ አገልግሎቱን ለመጀመር የባቡር መስመር ዝርጋታ እየተጠበቀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በነዳጅ ችርቻሮ ንግድ ላይ ለመሰማራት አራት ኩባንያዎች ፈቃድ ወሰዱ

በአገሪቱ የነዳጅ ችርቻሮ ንግድ ላይ የሚሰማሩ ኩባንያዎችን ቁጥር ወደ 22 የሚያሳድጉ አራት አዳዲስ አገር በቀል የነዳጅ ኩባንያዎች፣ ወደ ገበያ ሊያስገባቸው የሚችል ፈቃድ መውሰዳቸው ተገለጸ፡፡ በተመሳሳይ ሥራ ለመሰማራት የሚፈልጉ ሌሎች ኩባንያዎች ጥያቄ እያቀረቡ ነው፡፡

ጎመጁ ኦይል ተንቀሳቃሽ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች አስገባ

የነዳጅ ማከፋፈል ኢንዱስትሪን በቅርቡ የተቀላቀለው ጎመጁ ኦይል የተሰኘው አገር በቀል ኩባንያ፣ አገሪቱ ውስጥ ያለውን የነዳጅ ማደያ እጥረት ለመቅረፍ እንደሚረዱ የታመነባቸውን ስድስት ተንቀሳቃሽ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ገዝቶ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አገር ውስጥ አስገባ፡፡

ነዳጅ ድርጅት የአንድ ዓመት ነዳጅ ግዥ ውል ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለ2010/2011 በጀት ዓመት ፍጆታ የሚውል የነዳጅ አቅርቦት ስምምነት ትራፊጉራ ከተሰኘ የስዊዘርላንድ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኩዌትና ሱዳን መንግሥታት ጋር በገባው ውል መሠረት አብዛኛውን ነዳጅ የሚገዛው ከሁለቱ አገሮች ሲሆን፣ የተቀረውን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በየዓመቱ በሚያወጣው ዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ ይገዛል፡፡

የብር ምንዛሪ ለውጥ የነዳጅ ዋጋ ያንራል የሚል ሥጋት ፈጥሯል

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በብር ምንዛሪ ላይ ያደረገው የ15 በመቶ ለውጥ የነዳጅ ዋጋ ያንራል የሚል ሥጋት ፈጥሯል፡፡ ብሔራዊ ባንክ የተዳከመውን ኤክስፖርት ዘርፍ እንዲያንሠራራ ለማድረግ የብር ምንዛሪ በ15 በመቶ እንዲጨምር አድርጓል፡፡ ዕርምጃው የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎችን አስደንግጧል፡፡ የምንዛሪ ለውጡ በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ እንደሚፈጥር፣ በገቢና በአገር ውስጥ ምርቶች ላይ ዋጋ ጭማሪ በመፍጠር የኑሮ ውድነቱን ያባብሳል የሚል ሥጋት ፈጥሯል፡፡