Skip to main content
x

ዕጣ በወጣባቸው የ40/60 ቤቶች ውል እንዳይፈጸምና አዲስ ዕጣ እንዳይወጣ ዕግድ ተጣለ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ የወጣባቸውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ዕጣ የወጣላቸው ዕድለኞች ክስ ከተመሠረተባቸው መንግሥታዊ ተቋማት ጋር ውል እንዳይፈጽሙ ዕግድ ጣለ፡፡

ዕጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለዕድለኞች እንዳይተላለፉ የቀረበው የዕግድ ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም  

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ ያወጣባቸው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ለባለዕድለኞች መተላለፋቸው ታግዶ እንዲቆይ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አጣ፡፡

በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳቢያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተከሰሱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ ካወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ምክንያት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒቴርና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ተመዝጋቢዎች መቆጠብ ያለባቸው የገንዘብ መጠን ይፋ ሆነ

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ በሚወጣባቸው 18,576 የ40/60 ባለ አንድ፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱት ተመዝጋቢዎች፣ እስካሁን መቆጠብ ያለባቸው 40 በመቶ የገንዘብ መጠን ይፋ ሆኗል፡፡

በ40/60 የቤቶች ፕሮግራም መቶ በመቶ የቆጠቡ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩን አዲስ አቋም ተቃወሙ

በ40/60 የቤቶች ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነቡ ቤቶችን በቅድሚያ ለማግኘት ፕሮግራሙ ይፋ በተደረገበት ወቅት በተቀመጠው መሥፈርት መሠረት መቶ በመቶ ቁጠባ ፈጽመናል ያሉ ነዋሪዎች፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ቤቶቹን መቶ በመቶ የቆጠቡ ቅድሚያ የማግኘት መብት ሊኖራቸው አይገባም በማለት በያዘው አቋም ላይ ተቃውሞ አቀረቡ።

የአዲስ አበባ መሥሪያ ቤቶችን ቅርፅ የሚለውጥ መዋቅር ለምክር ቤት ቀረበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 114 መሥሪያ ቤቶችን ቅርፅና ይዘት በከፍተኛ ደረጃ የሚለውጥ አዲስ መዋቅር ለከተማው ምክር ቤት ቀረበ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ቀኑ ካልተለወጠ በስተቀር በመዋቅሩ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ለማሳለፍ ለታኅሳስ 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ተጠርቷል፡፡

በኢንሳ ሶፍትዌር ምክንያት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ማውጫ ቀን ተራዘመ

ሥልጣን ከያዘበት ከሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በበርካታ ሥራዎች የተጠመደው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ በኢትዮጵያ መረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ ማውጫ ሶፍትዌር ላይ ችግር መኖሩን በማስተዋሉ፣ የቤቶችን ዕጣ ማውጫ ቀነ ገደብ ለማራዘም መገደዱን አስታወቀ፡፡

የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ቤታቸውን ራሳቸው እንዲገነቡ የሚያስችል ጥናት ተጀመረ

በ20/80 እና በ40/60 ቤቶች ግንባታ እየተፈተነ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሒደት ከመኖሪያ ቤቶች ግንባታ በመውጣት፣ በአግባቡ እየቆጠቡ የሚገኙ ተመዝጋቢዎች የራሳቸውን ቤቶች እንዲገነቡ መሬት ማቅረብ የሚያስችል ጥናት ጀመረ፡፡