Skip to main content
x

የብሔራዊ ባንክ ገዥና የፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎች በአዳዲስ አመራሮች ሊተኩ ነው

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማትን ሪፎርም ለማድረግ እየተደረጉ ባሉ እንቅስቃሴዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኃላፊዎች በአዳዲስ አመራሮች ሊተኩ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ከኃላፊነታቸው እንደሚነሱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ አሁን ባለው መረጃ እሳቸውን ለመተካት የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነር ይናገር ደሴ (ዶ/ር) በዕጩነት ቀርበዋል፡፡

ንግድ ባንክ አስተዳደራዊ የመዋቅር ለውጥ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስካሁን ሲሠራበት የነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ ለውጥ አደረገ፡፡ በዚህም መሠረት የባንኩ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት መዋቅሮች ላይ ማሻሻያ አድርጓል፡፡ በማሻሻያውም የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉን ዘለቀ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሎ የሰየመ ሲሆን፣ በሥራቸውም ስምንት ሥራ አስፈጻሚዎችን አስቀምጧል፡፡

ፓስፖርት ለማውጣት የሚጠየቀው ክፍያ በንግድ ባንክ በኩል መስተናገድ ጀመረ

በርካታ ተገልጋዮችን ከሚያስተናገዱ መንግሥታዊ ተቋማት አንዱ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምርያ በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣትም ሆነ ለማሳደስ ብሎም ለመምርያው በሕግ የተሰጡትን ሌሎች የአገልግሎቶች ሰጪነት ድርሻዎችን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ እንዲህ ያሉትን አገልግሎቶች የሚሹ ተገልጋዮች ቁጥር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ እየታየ ነው፡፡ ተገልጋዮች በወረፋ ተሠልፈው ለሰዓታት የሚጠባበቁበት ይህ ተቋም፣ ከአራት ዓመታት በፊት በአንድ ቀን በአማካይ ከ1,200 በላይ ተገልጋዮችን ለማስተናገድ ይገደድ ነበር፡፡

በፋይናንስ አቅርቦት ችግር የ15 ባለ ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ እየተጓተተ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ 15 ባለ ኮከብ ሆቴል ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ ቢሆንም፣ ብድርም ሆነ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ መሆኑ ታወቀ፡፡ ከኢትዮጵያ ሚሊኒየም ወዲህ በርካታ ሆቴሎች በአዲስ አበባ የተገነቡ ሲሆን፣ አሁንም በርካታ የሆቴል ፕሮጀክቶች በማያቋርጥ የግንባታ ሒደት ላይ ይገኛሉ፡፡

በጎማና በብረት ዋጋ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታየ

በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት የኢንዱስትሪ ምርቶች በሆኑት ጎማና ብረት ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየታየ ነው፡፡ አገር በቀል የብረት ፋብሪካዎች ከአቅማቸው በታች እያመረቱ በመሆኑ በማምረቻ ዋጋቸው ላይ ከፍተኛ ግሽበት እንዳጋጠማቸው እየተናገሩ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አቢሲኒያ ባንክ በተከሰሱበት የፍትሐ ብሔር ክስ ላይ ሰበር ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ያላግባብና ከሕግ ውጪ ፈጽመዋል በተባለ የመጋዘን ጨረታና ሽያጭ፣ በናይል ቡና ላኪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የቀረበባቸውን የፍትሐ ብሔር ክስ ላለፉት 13 ዓመታት ሲከራከሩ ከርመው ጉዳዩ ሰበር ሰሚ ችሎት የደረሰ ቢሆንም፣ ችሎቱ ጉዳዩ በሥር ፍርድ ቤት በድጋሚ መታየት እንዳለበት ገልጾና የመከራከርያ ነጥቦችን ለይቶ በማስቀመጥ ውሳኔ ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

የደቡብና የኦሮሚያ ክልል ቡና አቅራቢዎች ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ የባንክ ዕዳ እንዲሰረዝላቸው ጠየቁ

ደቡብ ክልልና በኦሮሚያ የጉጂ ዞን የሚገኙ ቡና አጣቢዎች፣ አበጣሪዎችና አቅራቢዎች፣ ለዓመታት የተከማቸባቸውን ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የባንክ ዕዳ መንግሥት እንዲሰርዝላቸው ጠየቁ፡፡ የብድር ዕዳውን በወቅቱ መክፈል ያልቻሉት መንግሥት በተለያየ ጊዜ ባካሄዳቸው የፖሊሲ ለውጦች ሳቢያ በደረሰባቸው ኪሳራ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ንግድ ባንክ ‹‹ሲቢኢ ብር›› የተሰኘ የሞባይል ክፍያ አገልግሎት ጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‹‹ሲቢኢ ብር›› በማለት የሰየመውንና የሞባይል ስልክን መሠረት በማድረግ የሚሰጠውን የባንክ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታወቀ፡፡ ለዚህ አገልግሎት ከ2,600 በላይ ወኪሎችና ከ1,350 በላይ ተቋማትን እንደመለመለ ገልጿል፡፡

ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርን ሙሉ ለሙሉ ተረክቦ ማስተዳደር ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲያስተዳድረው ከነበረው የቻይና ኩባንያ ተረክቦ፣ በራሱ ማስተዳደር ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡