Skip to main content
x

በአዳማ ከፕላስቲክ የውኃ ጠርሙሶች ቪላ ቤት ተገነባ

ሲምኮን ቴክኖሎጂስ የተባለ አገር በቀል ኩባንያ፣ አገልግሎታቸውን የጨረሱ  የውኃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ጠርሙሶችን በመጠቀም ያስገነባውን ዘመናዊ ቪላ ቤት ለአገልግሎት አበቃ፡፡ ኩባንያው ለአገሪቱ እንግዳ የሆነውንና ለአካባቢ ጥበቃ ፋይዳ ያለውን አሠራር በመጠቀም፣ ከተጣሉ የውኃ መያዣ ፕላስቲክ ጠርሙሶች የተሠራው ሞዴል ቪላ ቤት የተገነባው በአዳማ ከተማ ነው፡፡ የፕላስቲክ ጠርሙስ ቪላ ቤቱ ሐሙስ፣ የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሕዝብ ዕይታ ይፋ በተደረገበት ወቅት እንደተገለጸው፣ በመቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ቪላ ቤት፣ ለግንባታው ከ53 ሺሕ በላይ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን ጠይቋል፡፡ የቪላ ቤቱን ግንባታ ለማጠናቀቅ የጠየቀው አጠቃላይ ወጪ 345 ሺሕ ብር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ግንባታውን ለማጠናቀቅም ሦስት ሳምንታት ብቻ እንደፈጀ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

ባለታሪኮችን ከመንገድና አደባባይ ጋር ያገናኘችው አዳማ

ከተመሠረተች ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረችው አዳማ (ናዝሬት) ከተማ በለውጥ ሒደት ውስጥ ትገኛለች፡፡ የምሥራቁን ክፍል ከመሀልና ከምዕራብ ጋር የምታገናኘው የንግድና ኢኮኖሚ ማዕከሏ አዳማ ከዓመት በፊት በአንድ አስተዳደር ብቻ ትመራበት የነበረው አካሄድን በስድስት ክፍላተ ከተማ መለወጧ አንዱ ተጠቃሽ ነው፡፡

ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ሦስት ሆቴሎችን እየገነባ ነው

በአምስት ዓመት ሆቴሎችን ብዛት 20 ለማድረስ አቅዷል ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በአርባ ምንጭ፣ አዲስ አበባና በአዳማ ሦስት ዘመናዊ ሆቴሎችን በመገንባት ላይ ነው፡፡ ከስምንት ዓመት በፊት ኃይሌና ዓለም ኢንተርናሽናል የኢንቨስትመንት ኩባንያው የሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርትን በመገንባት ወደ ሆቴልና ቱሪዝም መስክ የተቀላቀለ ሲሆን፣ በዝዋይና በሻሸመኔ ሁለት ሪዞርት ሆቴሎችን ከፍቷል፡፡ በሱሉልታ ከተማ ያያ ቪሌጅን ገንብቶ አገልግሎት ላይ ማዋሉ ይታወሳል፡፡