Skip to main content
x

በኢትዮ-ኤርትራ የጎዳና ሩጫ በርካታ ተሳታፊ ይጠበቃል

የኢትዮጵያና የኤርትራን ዳግም ወደ ሰላም መመለስ ተከትሎ በኢትዮ-ኤርትራ የሰላም፣ የአንድነትና የፍቅር የጎዳና ሩጫ በርካታ ተሳታፊዎች እንደሚጠበቁ ተገለጸ፡፡ የሁለቱን አገሮች ዕርቅና በመንግሥታቱ መካከል የነበረው ቁርሾ በሰላም መፈታቱን ተከትሎ፣ ሕዝቡን ከሕዝብ በስፖርትና በጥበብ ለማገናኘት ታስቦ ሩጫው መዘጋጀቱ ዓርብ ጥቅምት 2 ቀን 2011 ዓ.ም. በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተመልክቷል፡፡

አትሌቲክሱና አበረታች ቅመሞች

ኢትዮጵያ በዓለም የውድድር መድረኮች ከምትወከልባቸው ስፖርቶች አትሌቲክስ በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና ስፖርቱ አሁን አሁን የአገሮችን ስምና ዝና ከፍ እንዲል ከማስቻሉ ጎን ለጎን ለተወዳዳሪዎቹ የሚሰጠው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍ እያለ መምጣቱን ተከትሎ፣ አትሌቶች አሸናፊ ለመሆን በሚያደርጉት ጥረት ተጨማሪ ኃይል የሚጠቀሙበት ዕድል እየሰፋ መምጣቱ አሳሳቢ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

ለወጣቶች ኦሊምፒክ የተመረጡ አትሌቶች ዝግጅታቸውን አጠናቀቁ

ደቡብ አሜሪካዊቷ የእግር ኳስ አገር አርጀንቲና በምታስተናግደው የዓለም ወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ ለመሳተፍ የተመረጠው የኢትዮጵያ ወጣት የአትሌቲክስና የብስክሌት ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻው የዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጨምሮ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች የወጣቶቹን የዝግጅት ሒደት ጎብኝተዋል፡፡

በርሊን ያነገሠችው የኤልዶሬት አካዴሚ ፍሬ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) በወርቅ ደረጃ ከሚመድባቸው ማራቶን ተጠቃሽ ነው፡፡ አሸናፊዎች ረብጣ ዶላር የሚያሳፍሰው ዓመታዊው የበርሊን ማራቶን ባለፈው እሑድ ሲከናወን በሁለቱም ጾታ በኬንያውያን አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በሪዮ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ያስመዘገበው ሌሊሳ ፈይሳ ወደ አገር ቤት እንዲመለስ ጥሪ ተደረገለት

ከሁለት ዓመት በፊት ብራዚል ባስተናገደችው የሪዮ ኦሊምፒክ ላይ አትዮጵያ በማራቶን ወክሎ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ነበር፡፡ አትሌቱ በወቅቱ በአገሪቱ የነበረውን ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመቃወም እጆቹን አመሳቅሎ የተቃውሞ ምልክት በማሳየት በዚያው መቅረቱና ቆይቶም ወደ አሜሪካ ማቅናቱ አይዘነጋም፡፡

ኢትዮጵያ በአልጀርሱ የአፍሪካ ወጣት ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያዋ እየጨመረ ነው

በአልጀሪያ አልጀርስ ከሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 3ኛው የአፍሪካ ወጣት ጨዋታዎች፣ ኢትዮጵያ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በብስክሌትና ጠረጴዛ ቴኒስ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች፡፡

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ19 የውድድር ዓይነቶች ትሳተፋለች

21ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ  ለአምስት ቀናት በናይጀሪያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡ ኢትዮጵያ በ19 የውድድር ዓይነቶች ለመሳተፍ ብሔራዊ የአትሌቲክስ ቡድኑ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ሥፍራው ይጓዛል፡፡

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከመጪው ዓመት ጀምሮ ክለቦችና ቡድኖች ስያሜያቸው ከዘርና ከማንነት ካልራቀ ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አስታወቀ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኢትዮጵያ በሚካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች የሚሳተፉ ክልሎችም ሆኑ ክለቦች ስያሜያቸው ከዘርና ከማንነት ንክኪ የራቁ ካልሆኑ  ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ በ2018 የአፍሪካ ወጣት ጨዋታዎች 56 አትሌቶችን ታሳትፋለች

ኢትዮጵያ በአልጄሪያ መዲና አልጀርስ በሚከናወነው 3ኛው የአፍሪካ ወጣት ጨዋታዎች በስድስት ስፖርቶች 56 አትሌቶችን ታሳትፋለች፡፡ ጨዋታዎቹ በ20 ስፖርቶች በተለያዩ የውድድር ዓይነቶች የሚካሄዱት ከሐምሌ 11 ቀን እስከ 21፣ 2010 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡