Skip to main content
x

የነዳጅ ሠልፉን ምን አመጣው?

ለወትሮው የትራፊክ ትርምስ የሚያጨናንቃቸው የአዲስ አበባ ጎዳናዎች፣ ይህንኑ መጨናነቅ ያባባሰ ክስተት እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ የነዳጅ ማደያዎች በሚገኙባቸው ጎዳናዎች ላይ የሚታዩት የተሽከርካሪዎች ሽንጣም ሠልፎች ችግሩን ከድጡ ወደ ማጡ አድርገውታል፡፡ ያልተለመደው ዝናብ ታክሎበት የከተማዋ የትራፊክ እንቅስቃሴ ከወትሮው ይልቅ አስገራሚ መጨናነቅ እያስተናገደ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ያጋጠመው የቤንዚን እጥረት ‹‹ሰው ሠራሽ›› እንደሆነ ተገለጸ

በተለያዩ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ነዳጅ ገበያ፣ ካለፈው ሳምንት ሰኞ ጥቅምት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ በተለይ በአዲስ አበባ የቤንዚን እጥረት ገጥሞታል፡፡ የተፈጠረውን እጥረት የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ‹‹ሰው ሠራሽ›› በማለት ሲገልጸው፣ የነዳጅ ዘርፍ ዋነኛ ተዋናዮች ደግሞ ቤንዚን ከወደብ ለማንሳት ረዥም ጊዜ በመውሰዱ የተፈጠረ ችግር ነው ብለውታል፡፡

ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የ2011-2012 ነዳጅ ግዥ ጨረታ አወጣ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለ2011-2012 በጀት ዓመት ፍጆታ የሚውል የነዳጅ ግዥ ጨረታ አወጣ፡፡ ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት ባወጣው ግልጽ ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ ኩባንያዎች የቴክኒክና የፋይናንስ ዕቅዳቸውን እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲያቀርቡ ጋብዟል፡፡

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ቀውስ የነዳጅ ኩባንያዎች ሥራ አቋርጠዋል

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው የፖለቲካና የፀጥታ ቀውስ ሥጋት የገባቸው በክልሉ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ የሚያካሂዱ ኩባንያዎች ሥራ ማቋረጣቸው ታወቀ፡፡ በክልሉ በተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋና ሌሎች አነስተኛ ከተሞች በተፈጠሩ ግጭቶች በርካታ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው፣ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች፣ ባንክና ቤተ ክርስቲያኖች መዘረፋቸውና መቃጠላቸው የሚታወስ ነው፡፡

የ70 ዓመታት የነዳጅ ፍለጋ ጥረት ፍሬ እያፈራ ነው

ላለፉት 70 ዓመታት በኦጋዴን ቤዚን ሲካሄድ የቆየው የነዳጅ ፍለጋ ሥራ ፍሬ እያፈራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ ፖሊጂሲኤል ፔትሮሊየም ኢንቨስትመንት የተባለው የቻይና ሂላላ በተባለው ሥፍራ ያገኘውን የተፈጥሮ ዘይት ሐሙስ ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. የሙከራ ምርት ማውጣት ጀምሯል፡፡

ኢትዮጵያ ድፍድፍ ነዳጅ ማውጣት ልትጀምር ነው

ኢትዮጵያ ከሐሙስ ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ድፍድፍ ነዳጅ ማውጣት እንደምትጀምር ታወቀ፡፡

ፖሊ ጂሲኤል የተባለው የቻይና ኩባንያ በሶማሌ ክልል ነዳጅና ጋዝ ለማውጣት መሰማራቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ነዳጅ በሚያወጣበት ስፍራ ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ከስድስት እስከ ስምንት ትሪሊዮን ኪዩቢክ ፊት እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

በኦጋዴን ካሉብና ሂላላ አካባቢዎች ፍለጋውን ሲያካሂድ የነበረው ይህ ድርጅት፣ ሐሙስ የሚወጣው ድፍድፍ ነዳጅ ወደ አዲስ አበባ ተጓጉዞ ለሲሚንቶ አምራቾች እንደሚከፋፈል ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትና ስሜክ በዱከም የሚገነባውን የነዳጅ ዲፖ ዲዛይን ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በዱከም ከተማ አቅራቢያ በከፍተኛ ወጪ ለመገንባት ያቀደውን ግዙፍ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዲፖ የዲዛይንና ፕሮጀክት ክትትል ሥራ ውል ስሜክ ኢንተርናሽናል ከተባለ የአውስትራሊያ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ፡፡

የነዳጅ ኩባንያዎች ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ መግባታቸውን አስታወቁ

በነዳጅ ማከፋፈል ሥራ የተሰማሩ ኩባንያዎች ለሚሰጡት አገልግሎት የሚከፈላቸው የትርፍ ህዳግ በጣም አነስተኛ መሆን፣ ለዘርፉ መቀጨጭ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን አስታወቁ፡፡ ቅዳሜ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢሊሊ ሆቴል የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመገምገም ባሰናዳው የምክክር መድረክ ላይ፣ የነዳጅ ኩባንያዎች ኃላፊዎች በተለያዩ ጊዜያት መንግሥት ለነዳጅ ኩባንያዎች የፈቀደው የትርፍ ህዳግ በጣም አነስተኛ መሆኑን በመግለጽ እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ዕርምጃ ባለመወሰዱ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመንግሥትና በነዳጅ አቅራቢዎች መካከል አዲስ አለመግባባት ተፈጠረ

አራቱ ትልልቅ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ኖክ፣ የተባበሩት፣ ቶታልና ኦይል ሊቢያ የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ያቀረበላቸውን አዲስ ውል አንቀበልም ማለታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ በመንግሥታዊ ነዳጅ ድርጅትና በግል ነዳጅ አቅራቢዎች መካከል አዲስ አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡