Skip to main content
x

አዲሱ የመሬት ኮርፖሬሽን ለልማት ተፈናቃዮች ይጠቅማል የተባለ ዕቅድ አዘጋጀ

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በመሀል አዲስ አበባ የሚገኙ ቁልፍ ቦታዎችን እንዲያለማ ሥልጣን የተሰጠው ‹‹የአዲስ አበባ ማዕከላትና ኮሪደሮች ኮርፖሬሽን››፣ ከነበሩበት ቦታ የሚፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደነበሩበት ተመልሰው የሚቋቋሙበትን መንገድ እንደሚከታተል ተመለከተ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ እንደገለጹት፣ የመልሶ ማልማት ሥራ የሚካሄድበት የአካባቢ ነዋሪዎችን አፈናቅሎ ሳይሆን አካቶ መሆን ይኖርበታል፡፡

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ሰፋፊ የማዕድን ቦታዎችን ከባለሀብቶች ሊነጥቅ ነው

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግሥት ከ20 ሔክታር በላይ የማዕድን ቦታዎችን የያዙ ባለሀብቶች ለክልሉ እንዲመልሱ አዘዘ፡፡ ቤንሻንጉል በወርቅና በዕምነበረድ ሀብት የሚታወቅ ክልል ነው፡፡ በተለይ በዳለቲ፣ በፀዳልና በመተከል አካባቢ የሚገኘው ነጭ ዕምነበረድ ከፍተኛ ተፈላጊነት አለው፡፡ በቅርቡ በክልሉ የወጣው መመርያ የዕምነበረድ አምራቾችን የሚመለከት እንደሆነ ታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤምባሲዎችን ካርታ ለማምከን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋገረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ ግንባታዎች መሬት ከሊዝ ነፃ ወስደው ሳያለሙ ለዓመታት አጥረው ያስቀመጡ 18 ኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ይዞታ ላይ በሚወሰደው ዕርምጃ ላይ፣ ባለፈው ሳምንት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋገረ፡፡

ለ29ኛው የመሬት ሊዝ ጨረታ አዲስ ሶፍትዌር እየተዘጋጀ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየወሩ መሬት በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ እንደሚያወጣ ቢደነግግም፣ ላለፉት ሰባት ወራት አንድም ጊዜ ጨረታ አላወጣም፡፡ የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ጨረታ ማውጣት ያልቻለው፣ ጨረታውን ግልጽ ለማድረግ ዘመናዊ አሠራር ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ ነው ብሏል፡፡ ለዚህም ሲባል አዲስ ሶፍትዌር እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል፡፡  

ኮማንድ ፖስቱ ሕገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል አሠራር ዘረጋ

በአገሪቱ በተፈጠረው አለመረጋጋት የመሬት ወረራ ሊካሄድ ይችላል በሚል ሥጋት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያስፈጽም የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በዚህ ተግባር የሚሠማሩ አካላትን በቀጥታ ተጠያቂ የሚያደርግ አሠራር መዘርጋቱን አስታውቋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለአገልግሎት መስጫ ተቋማት መሬት የሚቀርብበትን መንገድ እንደሚወስን ይጠበቃል

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣውን አዋጅ በድጋሚ ለማሻሻል ባዘጋጀው ረቂቅ፣ አገራዊ ፋይዳ ያላቸው አገልግሎት መስጫ ተቋማት መሬት የሚያገኙበትን መንገድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲወስን ክፍቱን መተውን አመለከተ፡፡ ከዚህ ጋር ነባር ባለይዞታዎች በአክሲዮን ማኅበር ተደራጅተው አካባቢያቸውን ለማልማት ሲጠይቁ መስተናገድ እንዲችሉ ማካተቱን አስታውቋል፡፡

የመሬት ሊዝ ጨረታ ሳይወጣ ስድስት ወራት ተቆጠሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየወሩ መሬት በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ እንደሚያወጣ የደነገገ ቢሆንም፣ ላለፉት ስድስት ወራት አንድም የመሬት ሊዝ ጨረታ አልወጣም፡፡ በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሥር የሚገኘው የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ለመጨረሻ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ ያወጣው፣ ባለፈው ዓመት ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር፡፡

ሚድሮክ አጥሮ የያዛቸው 11 ቦታዎች ካርታ እንዲመክን ተወሰነ

በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የሚገኙት ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በኩባንያዎቻቸው ተመዝግበው ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ 11 ቦታዎች ካርታ እንዲመክን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ውሳኔ፣ በከተማው አስተዳደር ካቢኔና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይሁንታ ካገኘ ተፈጻሚ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

ግንባታ ባላጠናቀቁ አልሚዎች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ከሚያዝያ 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለመጨረሻ ጊዜ ለአንድ ዓመት የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ከተራዘመላቸው ፕሮጀክቶች መካከል፣ አሁንም ሊጠናቀቁ ያልቻሉ በርካታ ፕሮጀክቶች በመኖራቸው ዕርምጃ መውሰድ የሚያስችል የውሳኔ ሐሳብ አቀረበ፡፡ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ጥር 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ለመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ፣ በከተማው ውስጥ በሊዝ ቦታ ወስደው ከሚያዝያ 2008 ዓ.ም. በኋላ የሊዝ ውል ማሻሻያ የተደረገላቸውና ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ዓመት የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ የተራዘመላቸው አሁንም ግንባታ ያላጠናቀቁ አልሚዎች በሁሉም ክፍላተ ከተሞች ተንሰራፍተው ይገኛሉ፡፡