Skip to main content
x

በፓርቲ ተፅዕኖ ሥር የወደቀውን የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ግንኙነት ተቋማዊ ለማድረግ የተዘጋጀ የፖሊሲ ማዕቀፍ ለፓርላማ ተላከ

በአሁኑ ወቅት በአንድ ፓርቲ ተፅዕኖ ሥር እንደወደቀ በይፋ የታመነበትን የፌዴራልና የክልል የመንግሥታት ግንኙነት ከፓርቲና ከግለሰቦች ተፅዕኖ በማላቀቅ፣ ተቋማዊ መሠረትና ሕጋዊ ሥርዓት እንዲኖረው ለማድረግ የተረቀቀ የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲፀድቅ ለፓርላማ ተላከ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግሥታት ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ›› የሚል መጠሪያ የተሰጠውን ይህንን የፖሊሲ ማዕቀፍ ያረቀቁት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የፌዴራል አርብቶ አደርና ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ናቸው፡፡

ዘንድሮ ሊካሄድ የነበረው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለሚቀጥለው ዓመት እንዲተላለፍ ተወሰነ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ምክር ቤት በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ፣ አራተኛው አገር አቀፍ የሕዝብና የቤት ቆጠራ እንዲራዘም ወሰኑ፡፡ የተወሰኑ አባላት በቀረበው የማራዘሚያ ሐሳብ ሕገ መንግሥታዊነት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። የጋራ ምክር ቤቱ የማራዘሚያ የውሳኔ ሐሳቡን ያፀደቀው በአንድ የተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ነው። በመሆኑም ዘንድሮ ይካሄዳል ተብሎ ዝግጅት ሲደረግበት የነበረው የሕዝብና ቤት ቆጠራ፣ በ2011 ዓ.ም. አመቺ በሆነ ወቅት እንዲካሄድ ተራዝሟል። 

ክልሎች በግል ባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች ላይ የገቢ ግብር እንዲጥሉ ተወሰነላቸው

ክልሎች በግል ባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች ላይ የገቢ ግብር እንዲጥሉ፣ ገቢውም የክልሎች እንዲሆን በመንግሥት መወሰኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ የምክር ቤቱ የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 21 እና 22 ቀን 2010 ዓ.ም. መደበኛ ጉባዔውን ላካሄደው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባቀረበው የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዳስታወቀው፣ በግል ባለቤትነት ሥር ካሉ ንብረቶች በሚገኝ ገቢ ላይ የፌዴራል መንግሥት ግብር በመጣል ገቢውን ለራሱ መሰብሰቡ ከሕገ መንግሥቱ የሚቃረን በመሆኑ፣ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ ገቢውን የመጣልና የመሰብሰብ ሥልጣን ለክልሎች እንዲሆን በመንግሥት ደረጃ መወሰኑን አመልክቷል፡፡

ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔውን አሰናብቶ በምትካቸው መረጠ

ላለፉት ሦስት ዓመታት በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ያለው አባተ ያቀረቡትን መልቀቂያ የተቀበለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በምትካቸው ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ባካሄደው መደበኛ ጉባዔው፣ ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አፈ ጉባዔ ያለው አባተ፣ ከአፈ ጉባዔነታቸው መነሳት እንደሚፈልጉ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሏል፡፡

ሕገ መንግሥቱን እንደገና መተርጎም አስፈላጊ መሆኑ የተብራራበት የውይይት መድረክ

ወ/ሮ ዓለሚቱ ገብሬ ነዋሪነታቸው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በከፋ ዞን በጊንቦ ወረዳ ነው፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት ሁለት ሔክታር መሬታቸውን አቶ ጫኔ ደሳለኝ ለሚባል ግለሰብ ለአምስት ዓመት እንዲጠቀምበት ያከራዩታል፡፡ አቶ ጫኔ ኪራዩ 50 ዓመት ነው በማለት በይዞታው ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በማውጣት ይዞ እንደተገኘ፣ ወ/ሮ ዓለሚቱ ያቀረቡት አቤቱታ ያስረዳል፡፡ በዚህም መሬቴን ይልቀቅልኝ ሲሉ ለጊምቦ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ ይመሠርታሉ፡፡

የፓርላማ ሕንፃዎችን ለመገንባት የወጣው የቢሊዮን ብሮች ጨረታ አገር በቀል ኮንትራክተሮችን አስቆጣ

ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሁሉን ዓይነት አገልግሎቶች የሚሰጡ ግዙፍ ግንባታዎችን ለማካሄድ የወጣው ጨረታ፣ የኢትዮጵያ ደረጃ አንድ ሥራ ተቋራጮች ማኅበርን አስቆጣ፡፡

ምልዓተ ጉባዔ ለጥቂት ተሟልቶ የተካሄደው የፓርላማ ውሎ

የከተማ ፕላን ረቂቅ አዋጅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ተመርቷል ፓርላማው ሐሙስ ኅዳር 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የነበረውን መደበኛ ስብሰባ ለማካሄድ የሚያስፈልገውን ምልዓተ ጉባዔ ለጥቂት በማሟላት፣ ለዕለቱ በያዛቸው ሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ሕገ መንግሥታዊነትን የማረጋገጥ ጫናና ዝግጁነት

የ1987 ዓ.ም. የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ሥራ ላይ ከዋለ 22 ዓመታት አለፉ፡፡ ሕገ መንግሥቱ ከመሠረታዊ መብቶች ጋር ስምሙ የሆነ የሕግና የፖለቲካ ሰነድ እንደሆነ ብዙዎች ቢስማሙም፣ በተግባር ላይ ስለመዋሉ ወይም ሕገ መንግሥታዊነቱ ስለመረጋገጡ፣ ወይም ለሰብዓዊ መብት መረጋገጥ ዋስትና የመሆኑ ጉዳይ ግን አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

አወዛጋቢዎቹ የአማራና የቅማንት አራት የጋራ ቀበሌዎች ላይ ውሳኔ ተላለፈ

ውዝግብ የተፈጠረባቸው የአማራና የቅማንት ማኅበረሰቦች ተቀላቅለው ይኖሩባቸው የነበሩ አራት ቀበሌዎች ላይ ውሳኔ ተላለፈ፡፡ በአማራ ክልል የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየልኝ ሙሉዓለም ዓርብ ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በአማራና በቅማንት ማኅበረሰቦች መካከል ውዝግብ በመፈጠሩ ምክንያት መስከረም 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ያልተካተቱት የአራቱ ቀበሌዎች ዕጣ ፋንታ ውሳኔ አግኝቷል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልና የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ የነበሩ ግለሰብ ተከሰሱ

በሶማሌ ክልል በተለያዩ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ በተለይም የፕሬዚዳንቱ አማካሪ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልና የሊበን ዞን መስተዳድር ምክትልና ዋና ኃላፊ በመሆን ይሠሩ የነበሩት አቶ መሐመድ መሐሙድ አደን ኢልሚ ክስ ተመሠረተባቸው፡፡