Skip to main content
x

የኬሚካሎች ብክለት ሥጋት እየጨመረ ነው

ከአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተያይዞ የኬሚካሎች ዝውውርና ክምችት እየተስፋፋ በመሄዱ፣ የተለያዩ ኬሚካሎች ብክለት ሥጋት እየጨመረ እንደመጣ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በጁፒተር ሆቴል በተከፈተው ዓለም አቀፍ የኬሚካል ደኅንነትና አስተዳደር ጉባዔ ላይ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ የኬሚካል መሣሪያዎች መከላከል ድርጅት ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ባለው ሥልጠና፣ አገሮች ጅምላ ጨራሽ ኬሚካል መሣሪያዎችንና አደገኛ ኬሚካሎችን እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ ሰፊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር ጥረት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዋ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪውን የ2010 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡ ሐሙስ ነሐሴ 10 ቀን 2010 ዓ.ም.

አነስተኛና መካከለኛ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማስፋፋት የተያዘው ዕቅድ የበጀት ችግር ገጠመው

ከግዙፍ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር ተመጋጋቢ የሚሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ለማቋቋም የተቀረፀው ፕሮጀክት፣ የሚጠይቀውን ፋይናንስ ማግኘት አለመቻሉ ታወቀ። በፌዴራል መንግሥት የተቀረፀው ይህ ፕሮጀክት በባለቤትነት ተግባራዊ እንዲሆን የሚፈለገው በክልል መንግሥታት ነው፡፡

አገር በቀል አምራቾች ብሔራዊ ባንክ እነሱን ያገለለ ለውጭ ኩባንያዎች ብቻ የሚስማማ መመርያ ተግባራዊ ማድረጉን ተቃወሙ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የውጭ አቅራቢዎች የዱቤ ሽያጭ መመርያ፣ አገር በቀል አምራቾችንን ያገለለና የውጭ ባለሀብቶች እንደ ልባቸው ጥሬ ዕቃና ሌሎችም ግብዓቶችን ማስገባት እንዲችሉ የሚያስችላቸው ነው ሲሉ የአገር ውስጥ አምራቾች ተቃውሞ አሰሙ፡፡ በመመርያው መደናገጣቸውን በመግለጽ ጭምር አቤቱታቸውን ለመንግሥት አቅርበዋል፡፡

የቻይናው ሹራብ አምራች አሥር ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስገኝ የሚጠበቀውን ፋብሪካ ሥራ አስጀመረ

በቻይናው ሻንቴክስ ሆልዲንግ ግሩፕ ሥር ከሚተዳደሩ በርካታ ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ በመሆን በኢትዮጵያ ሥራ የጀመረው ሎንቶ ጋርመት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ በዓመት አሥር ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ ሊያስገኝ እንደሚችል የሚጠበቀውን ፋብሪካ በዱከም መሥርቷል፡፡ ቅዳሜ ሚያዝያ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. የፋብሪካው የምርቃት ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል፡፡

የግሉ ዘርፍ በባዮፊዩል ልማት እንዲሳተፉ ተጠየቀ

በባዮፊውል ልማት የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንዲሠራ ጥሪ ቀረበ፡፡ የአቪዬሽን ባዮፊውል ጉባዔ ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን በሒልተን ሆቴል ሲካሄድ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ መብራህቱ መለስ (ዶ/ር)፣ መንግሥት የባዮፊውል ልማት በሰፊው ለመሥራት ከፍተኛ ቁርጠኝነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንዲሠራ ፍላጎት እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

አራት የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮችን ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት እየተካሄደ ነው

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት በነደፈው ዕቅድ መሠረት የመጀመርያዎቹ አራት የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮችን ለመገንባት ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት እንደሚያስፈልግ ባለፈው ዓመት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ ይኼንን ተከትሎም ሲከናወኑ ከነበሩ ሥራዎች ውስጥ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮቹን ዕውን ለማድረግ የሚረዱ የአዋጭነት ጥናቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምርታማነትን እየጎዳ ነው

የውጭ ምንዛሪ እጥረት የአምራች ኢንዱስትሪውን እግር ከወርች ይዞ አላላውስ እንዳለ የተለያዩ ፋብሪካዎች ገለጹ፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር የተፈጠሩ ችግሮች ለከፍተኛ ችግር እንደዳረጓቸው አምራቾች ለፌዴራል መንግሥት አስታውቀዋል፡፡ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው የምክክር መድረክ፣ የተለያዩ ፋብሪካዎች ባለቤቶችና ተወካዮች በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ምርታማነታቸው እንዳሽቆለቆለና ህልውናቸው አደጋ ውስጥ እንደገባ ገልጸዋል፡፡

የንግድ ምክር ቤት አባልነት በውዴታ ወይስ በግዴታ?

የንግድ ምክር ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 341/1995 ለማሻሻል ከተለያዩ አካላት የመነሻ ሐሳቦች ቀርበው እየተመከረባቸው ናቸው፡፡ ከ70 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላቸው ንግድ ምክር ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 314/1995 መሠረት እንደ አዲስ ሲደራጁ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት የሚል መጠሪያ ይዘው እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡ ይሁንና በዚህ አዋጅ መሠረት ከተደራጁ በኋላ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ሲብላሉ ቆይተው አዋጁን ለማሻሻል ወደሚያስችሉ ተግባሮች እየገባ ነው፡፡

የንግድ ምክር ቤቶች መቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የቀረቡ ሁለት ሐሳቦች እየተፋጩ ነው

በመላ አገሪቱ የሚገኙትን የንግድ ኅብረተሰብ ይወክላሉ የተባሉ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ከግማሽ ሚሊዮን ያላነሱ አባላትን እንደያዙ ይነገራል፡፡ እነዚህ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ቀድሞ በንግድ ምክር ቤት አሁን ደግሞ በንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች የሚል መጠሪያ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ይሁንና እነዚህን ተቋማት ከ12 ዓመታት በፊት እንደ አዲስ እንዲዋቀር ያደረገው አዋጅ ቁጥር 341/95 ከወጣበት ጊዜ አንስቶ አዋጁ በርካታ ክፍተቶች እንዳሉት ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡ በተለይም ዘርፍ ምክር ቤቶች ከታች ጀምሮ በራሳቸው መዋቅር እንዲደራጁና በየደረጃው ከንግድ ምክር ቤቶች ጋር ተጣምረው እንዲደራጁ መደረጉ፣ የንግድ ምክር ቤቶችን እንቅስቃሴ በተፈለገው ደረጃ አላራመደም በሚል የተለያዩ መከራከሪያዎች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡