Skip to main content
x

ከውጭ የተገዙ ምርቶች በተመሳሳይ ወቅት ጂቡቲ በመድረሳቸው የትራንስፖርት መጨናነቅ ተፈጠረ

መንግሥት ከውጭ በገፍ የገዛቸው ምርቶች በተመሳሳይ ወቅት ጂቡቲ ወደብ በመድረሳቸው፣ በተለይ ከወደብ እስከ ጋላፊ ያለው መንገድ ክፉኛ በመበላሸቱ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንደተፈጠረ ተመለከተ፡፡ መንግሥት ለ2010/2011 ዓ.ም. ምርት ዘመን የሚያስፈልግ 1.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በ600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ግዥ እየፈጸመ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ገበያ ለማረጋጋት 200 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ በ1.6 ቢሊዮን ብር በሚሆን ወጪ፣ እንዲሁም 400 ሜትሪክ ቶን ስኳር በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡

ለስንዴ እጥረት ምክንያት የሆነው ዓለም አቀፍ ግዥ አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል

ለአገራዊ የስንዴ እጥረት መፈጠር ምክንያት የሆነው የ400 ሺሕ ቶን ስንዴ ግዥ አሁንም አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ስድስት ወራት ሙሉ የተጓተተው የስንዴ ጨረታ ገዥውን አካል ማለትም የመንግሥት ግዥዎችና ንብረት ማስወገድ አገልግሎትን ለወቀሳ ዳርጎታል፡፡ ከዚህ ቀደም ጨረታው በወጣበት ጊዜ ሻኪል የተባለ የፓኪስታን ኩባንያ 2.6 ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ ጨረታውን አሸንፎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ዳቦ ያሳጡ አንጀት ይልጡ

መንግሥት መሠረታዊ የሚባሉ እንደ ስንዴ፣ ዱቄት፣ ዳቦ፣ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉት ምርቶችን ሥርጭትና ግብይት በመቆጣጠር እንዲገበያዩ ያደርጋል፡፡  ይህን የሚያደርገውም እንዲህ ያሉትን መሠረታዊ ሸቀጦች በዋጋ እየደጎመ ማቅረቡን በመከራከሪያነት በማቅረብ ነው፡፡ ለዓመታት በዚህ መንገድ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህ የድጎማ አሠራር በዚህ መንገድ እንዲካሄድ ታምኖበት እየተተገበረ ይገኛል፡፡

የስንዴ እጥረትን ለመቅረፍ ከመጠባበቂያ ክምችት 70 በመቶው መሠራጨቱ ተገለጸ 

መንግሥት 800 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ከውጭ ለማስገባት ጨረታ ቢያወጣም፣ በተደጋጋሚ የጨረታው ውጤት በመሰረዙ ምክንያት በአገሪቱ የስንዴ አቅርቦት እጥረት ተከስቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ከዚህ ቀደም ከመጠባበቂያ ክምችቱ 200 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ሲሰራጭ ቢቆይም፣ መንግሥት በቅርቡ የ300 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ተጨማሪ ስንዴ ከመጠባበቂያ በማውጣት ለማሰራጨት ተገዷል፡፡

የስንዴ እጥረቱ የፈጠረው የገበያ አለመረጋጋት

ከስድስት ወራት በፊት ከሸማቾች ማኅበራት መደብሮች አንደኛ ደረጃ የሚባለውን የስንዴ ዱቄት  ከአሥር እስከ አሥራ ሁለት ብር፣ ሁለተኛ ደረጃ የሚባለውን ደግሞ በስምንት ብር መግዛት ይቻል ነበር፡፡ ከሦስት ወራት ወዲህ ግን በሸማቾች ማኅበራት መደብሮች ዱቄት እንደልብ ማግኘት ከባድ በመሆኑ፣ ሸማቾች የግድ ወደ ችርቻሮ መደብሮች መሄድ ግድ እንዳላቸው ይገልጻሉ፡፡

የኢትዮጵያ የእህል ምርት ከተገመተውም የተሻለ ውጤት እንደሚያሳይ የአሜሪካው የግብርና መሥሪያ ቤት ይፋ አደረገ

በአሜሪካው የግብርና መሥሪያ ቤት ዕውቅና ‹‹ግሎባል አግሪካልቸራል ኢንፎርሜሽን ኔትወርክ›› የተሰኘው ዓመታዊ ሪፖርት ውስጥ የተካተተው የኢትየጵያ የሰብል ምርት መጠን፣ የግብይትና የፍጆታ ትንታኔ፣ ከዚህ ቀደም አነስተኛ ምርት እንደሚኖር የተገመተውን ያሻሻለ ትንበያ ቀርቦበታል፡፡

ሁለት ኩባንያዎች 400 ሺሕ ቶን ስንዴ ለማቅረብ ጨረታ አሸነፉ

400 ሺሕ ቶን ስንዴ ለመግዛት የወጣውን ጨረታ ፕሮሚሲንግ ኢንተርናሽናልና ኢንትሬድ የተባሉ ሁለት ኩባንያዎች በ3.3 ቢሊዮን ብር የመጫረቻ ዋጋ አሸነፉ፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት የተከፈተው ጨረታ ስድስት ዓለም አቀፍ የስንዴ አቅራቢዎች እንደተሳተፉበት ይታወሳል፡፡ በሦስት ሎቶች ተከፍፍሎ በወጣው ጨረታ ማለትም ሎት አንድ 200 ሺሕ ቶን፣ ሎት ሁለትና ሦስት እያንዳንዳቸው 100 ሺሕ ቶን እንዲይዙ ተደርጎ ጨረታው ወጥቷል፡፡

በስንዴ ዱቄት እጥረት የሚሰቃዩት የቤንሻንጉል ጉምዝ ነዋሪዎች

መንግሥት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግና የኑሮ ውድነት ግሽበትን ለመከላከል፣ ከፍተኛ ድጎማ በማድረግ፣ በተመጣጣኝና አነስተኛ ዋጋ የስንዴ ዱቄት፣ ስኳርና ዘይት እንዲከፋፈሉ የዘረጋው አሠራር ቢኖርም፣ እየደረሳቸው እንዳልሆነ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ለ400 ሺሕ ቶን ስንዴ ግዢ 3.2 ቢሊዮን ብር የመጫረቻ ዋጋ ቀረበ

መንግሥት 400 ሺሕ ቶን ስንዴ ለመግዛት ባወጣው ጨረታ ኢንትሬድ የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ለአንድ ቶን ስንዴ 296 ዶላር ዝቅተኛ ዋጋ ሰጠ፡፡ ማክሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ረፋድ ላይ በተከፈተው ጨረታ ስድስት የዓለም አቀፍ የስንዴ አቅራቢዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ኢንትሬድ ያቀረበው አነስተኛ የመሸጫ ዋጋ የአጠቃላይ ስንዴውን መግዣ ዋጋ 3.19 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፡፡

መንግሥት 400 ሺሕ ቶን ስንዴ ሊገዛ ነው

መንግሥት 400 ሺሕ ቶን ስንዴ ከውጭ ሊገዛ ነው፡፡ ጨረታው በሚቀጥለው ሳምንት ይወጣል፡፡ ከኢትዮጵያ ንግድ ኮርፖሬሽን የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው ግዥውን ለማቅረብ ወደ ተቋሙ የሚመጣ ኩባንያ በሦስት ጭነቶች ስንዴውን እስከ መጪው የካቲት ወር አጓጉዞ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡