Skip to main content
x

በአዲስ አበባ ሪል ስቴት ለማልማት ሦስት ተቋማት ጥምረት ፈጠሩ

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ፋይናንስ የሚያደርገው የአሜሪካው የኢንቨስትመንት ኩባንያ ኤስጂአይ ፍሮንቲር ካፒታልና በሪል ስቴት ልማት የተሰማራው ሮክስቶን ሪል ስቴት ከቢጋር የግንባታና ሪል ስቴት አልሚ ኩባንያ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ለማልማት ጥምረት ፈጠሩ፡፡

የሪል ስቴትና የአከራይ ተከራይ አዋጅ በድጋሚ እንዲስተካከል ታዘዘ

በሪል ስቴት ቤቶች ግብይት፣ በመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩና በኅብረተሰቡ ዘንድ ተጠባቂ የሆኑ ሦስት ረቂቅ አዋጆች በጥቅል ተዘጋጅተው ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከቀረቡ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሦስቱም ረቂቅ አዋጆች ተነጣጥለው እንዲዘጋጁ በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ሙለር ሪል ስቴት የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እከሳለሁ አለ

የራስ አበበ አረጋይ መኖርያ ቤት ቅርስ ነው ተብሎ የተመዘገበ በመሆኑ መፍረስ አልነበረበትም በሚል ምክንያት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እየተካሄደ የነበረውን የአፓርትመንት ግንባታ እንዲታገድ ማድረጉን የተቃወመው ሙለር ሪል ስቴት፣ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደው አስታወቀ፡፡ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች የሚታወቀው ሙለር ሪል ስቴት ኩባንያ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ የራስ አበበ አረጋይ መኖርያ ነው የተባለው ቤት ከቤተሰቦቻቸው በሽያጭ ወደ ሌላ ግለሰብ የተዛወረና በተደጋጋሚም ተሸጦ የስም ዝውውር የተካሄደበት ነው፡፡ ሙለር ሪል ስቴትም ለሦስተኛ ጊዜ ለሽያጭ ሲቀርብ ገዥ ሆኖ በመቅረቡ በፍትሕ ሚኒስቴር የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽሕፈት ቤት በፀደቀ ውል የራሱ አድርጎ ካርታ መያዙን አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ የተንሰራፋውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኅብረተሰቡ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች ለመፍታት በ13 መሥሪያ ቤቶች ላይ ባካሄደው ጥናት፣ 211 ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ዝርዝር የመፍትሔ ሐሳቦችን አቀረበ፡፡

ከ250 በላይ የፍሊንትስቶን ሆምስ ቤት ገዥዎች በውላቸው መሠረት መረከብ አልቻልንም አሉ

‹‹የተባለው ሁሉ ትክክል ቢሆንም ችግሩ ግን የእኛ ብቻ አይደለም›› አቶ ፀደቀ ይሁኔ የፍሊንትስቶን ሆምስ ሥራ አስፈጻሚ ከአራት ዓመታት በፊት ከፍሊንትስቶን ሆምስ ጋር በሁለት ዓመታት ውስጥ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ እንደሚረከቡ ስምምነት ፈጽመው የነበሩ ቤት ገዥዎች፣ ውል ከፈጸሙበት የመረከቢያ ጊዜ ሁለት ዓመታት አሳልፈው ቤቱን በአራተኛው ዓመት ቢረከቡም በኤሌክትሪክ ኃይልና ባልተጠናቀቁ ግንባታዎች እየተሰቃዩ መሆኑን ገለጹ፡፡

የአክሰስ ሪል ስቴት ቤት ገዥዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ ልናቀርብ ነው አሉ

የሞግዚት አስተዳደር እንዲቋቋም ሐሳብ ያቀርባሉ በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ መሥራችነት ከተቋቋመው አክሰስ ሪል ስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሙሉ፣ ግማሽና የተወሰነ ክፍያ በመፈጸም ቤት የተመዘገቡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቤቱታቸውን ለማሰማት ፊርማ እያሰባሰቡ መሆኑን ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡