Skip to main content
x

ግርግር በመፍጠር በአገሪቱ የተጀመረውን የነፃነት ትግል ለማኮላሸት እንደማይቻል ኦፌኮ ገለጸ

በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ግርግር በመፍጠር ተጠቃሚ ለመሆን የሚሹ ኃይሎች በአገሪቱ የተጀመረውን የነፃነት ትግል ለማኮላሸት እንደማይችሉ፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አስታወቀ፡፡ መንግሥት ጥቃት በፈጸሙ ወንጀለኞችና ጥቃቶችን ቸልተኛ ሆነው ያለፉ የፀጥታ አካላት ላይ ዕርምጃ እንዲወስድም ጠይቋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰሞኑን ጥቃቶች አወገዙ

ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰንበቻውን በአዲስ አበባና በተለያዩ ሥፍራዎች የተፈጸሙ ጥቃቶችን አወገዙ፡፡ ፓርቲዎቹ ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ በአገሪቱ እያጋጣሙ ያሉ ግጭቶችና ጥቃቶች አሳሳቢና አሳዛኝ ናቸው ብለዋል፡፡

መንግሥት ከሰንደቅ ዓላማ ጋር የተያያዙ አለመግባባቶችን በአስቸኳይ እንዲያስቆም ፓርቲዎች ጠየቁ

በዓርማና ሰንደቅ ዓላማ እየተመካኘ የሚፈጠረው አምባጓሮ በአስቸኳይ እንዲቆምና ሁኔታዎች ከቁጥጥር በላይ ሆነው ወደ ሁከትና ብጥብጥ ከማምራታቸው በፊት መንግሥት አፋጣኝ የእርምት ዕርምጃ እንዲወስድ፣ ሰማያዊ ፓርቲና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በጋራ በሰጡት መግለጫ ጠየቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር መረራ ጉዲናን የኢቢሲ ቦርድ አባል አድርገው ሰየሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሙስ ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በርሳቸው ተፈርሞ በወጣ ደብዳቤ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲናን (ዶ/ር) ከሌሎች ሦስት ግለሰቦች ጋር የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል አድርገው ሰየሙ፡፡

የኦዴግና የኢሕአዴግ ድርድር በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር)፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ ከመረጠና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ከተሾሙ ሁለት ወራት ሊሞላቸው ከአንድ ሳምንት ያልበለጠ ጊዜ ብቻ ይቀራል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የስንብት ጥያቄ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሐሙስ የካቲት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ከኢሕአዴግ ሊቀመንበርነትና ከመንግሥት ኃላፊነት በራሳቸው ፈቃድ ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ማስታወቃቸው፣ የሰሞኑ አንዱ የአገሪቱ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን የመሰናበት ጥያቄ አገሪቱ በገጠማት የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት በመሆኑ፣ በሕዝቡ ውስጥ የተደበላለቁ ስሜቶች ተንፀባርቀዋል፡፡ ላለፉት ስድስት ዓመታት ያህል በኢሕአዴግ ሊቀመንበርነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሠሩት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ለሦስት ዓመታት ያህል መቆም ባልቻለው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት በደረሰ ጉዳት በርካቶች በመሞታቸው፣ በመጎዳታቸውና ከቀዬአቸው በመፈናቀላቸው ሳቢያ ሥልጣን ለማስረከብ መገደዳቸው ታውቋል፡፡ 

ከእስር ተፈቺዎች ብሔር ተኮር ጥቃትና የንብረት ውድመት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲቆም አሳሰቡ

በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ብሔር ተኮር ጥቃትና የንብረት ውድመት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም እንዳለበት፣ ሰሞኑን በይቅርታና ክስ በማቋረጥ ከእስር የተለቀቁ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች አሳሰቡ፡፡ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከተከሰቱ ግጭቶችና ሁከቶች ጋር በተገናኘ ብሔር ተኮር ዕርምጃ በመውሰድ ሕይወት እንዲያልፍ፣ የአካል ጉዳት እንዲደርስና ንብረት በቃጠሎና በተለያዩ ምክንያቶች እንዲወድም ማድረግ ኢትዮጵያዊነትን የማይገልጽና የሚያመጣውም አመርቂ ውጤት ስለማይኖር፣ መወገዝ ያለበት ድርጊት መሆኑን አክለዋል፡፡

ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ተቃውሞና እያስከተለ ያለው ጉዳት

ወጣት ሌንሳ ገመቹ ተወልዳ ያደገችው በኦሮሚያ ክልል ፊኒፊኔ ልዩ ዞን ሱሉልታ ከተማ ሲሆን፣ ወላጆቿ ሁለት ልጆች ብቻ መውለዳቸውንና እሷ የመጨረሻ ልጅ እንደሆነች ትናገራለች፡፡፡ በ1994 ዓ.ም. የአሥረኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ብትወስድም ውጤት እንዳልመጣላት ታስታውሳለች፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ መጀመር አለበት አሉ

ለ14 ወራት በእስር ከቆዩ በኋላ ሐሙስ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴራል ደረጃ ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጎ ከእስር ከተፈቱ 115 ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ በኢትዮጵያ አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ መጀመር አለበት አሉ፡፡ ዶ/ር መረራ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ሪፖርተር አነጋግሯቸው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ጃንሆይ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሲጀመርና ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ለቆ ሲወጣ ለሚመሩት ሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ‹አዲስ ዘመን ጀምረናል ብለው ነበር፡፡ አሁንም የኢሕአዴግ አራቱ ድርጀቶች ሊቃነ መናብርት በነካ እጃቸው ሌሎቹንም እስረኞች ፈትተው አዲስ የዴሞክራሲ ምዕራፍ መጀመር አለባቸው፤›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡