Skip to main content
x

ጣዕም ያጣው የ‹‹ሸገር ደርቢ›› ፉክክር

የኢትዮጵያ እግር ኳስ የሜዳ ውሎዎችና ክንውኖች ሥርዓት አልበኝነት ከነገሠባቸው ሰነባብተዋል፡፡ ለመካሪም ለዘካሪም የሚረቱ አልሆኑም፡፡ ሊጉን በበላይነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ በሜዳ ላይ በሚታዩ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰቶችና የዲሲፕሊን ግድፈቶች ላይ ቆንጠጥ ያሉ ዕርምጃዎችን መውሰድ ቢጀምርም፣ ድርጊቶቹ ሊገቱ ወይም አደብ ሊገዙ አልቻሉም፡፡

የወልዲያ ስታዲየም ለአንድ ዓመት ውድድር እንዳያስተናግድ መታገዱን ክለቡ ተቃወመ

  • አሠልጣኙና ተጫዋቾች ዕግድና የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የተመልካቾች አምባጓሮ በአብዛኞቹ ክልሎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ እየታየ ነው፡፡ በክልሎች በሚካሄዱ ውድድሮች ወቅት የተጫዋቾችንና የደጋፊዎችን ስም እየጠሩ መሳደብና ማንቋሸሽ፣ ብሽሽቁን ወደ ብሔር በመውሰድ ግጭት ማስነሳትና ድንጋይ መወራወር፣ ተጫዋቾችንና አሠልጣኞች ማስፈራራት በስታዲየሞች አካባቢ እየተለመደ መጥቷል፡፡ የአካል ላይ ጉዳት ማድረስና የንግድ ቤቶችን ማጥቃት እየተለመደ በመምጣቱ፣ ረብሻውን ለማረጋጋት አስለቃሽ ጋዝ እስከ መጠቀም ደረጃ ተደርሷል፡፡

ፊፋ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲመረጥ አዘዘ

ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አካል ፊፋ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫን የሚያስፈጽም አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ እንደገና እንዲያዋቅር ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

ፊፋ በፌዴሬሽኑ የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ላይ የነበረውን ውዝግብ ለመፍታት ውሳኔ እንደሚያተላለፍ ከሳምንታት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ፊፋ በደብዳቤው አዲሱ የአስመራጭ ኮሚቴ የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ልየታ እንደገና እንዲሠራና ወደ ምርጫ ሒደት እንዲገባም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የፌዴሬሽኑ ነዳጅ ማደያ ጨረታ ክርክር አስነሳ

ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የጨረታው አሸናፊ ቢታወቅም፣ ነገር ግን አሁንም ሒደቱ የመንግሥት የጨረታ አሠራርን የተከተለ አይደለም በሚል፣ ቅሬታ የሚያቀርቡ አልታጡም፡፡ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ምክንያት የሚሉትን ሲቀጥሉ፣ ጨረታው እንዲጓተት የቀድሞ ተከራይ ተብሎ የቀረበው ትክልል እንዳልሆነና አሠራሩም ‹‹በእከክልኝ ልከክልህ›› ዓይነት የተከናወነ ስለመሆኑ ጭምር ያስረዳሉ፡፡

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ምርጫ እንደገና ተራዘመ

ጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ሰመራ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚና የፕሬዚዳንት ምርጫ በድጋሚ ለአንድ ወር ተራዘመ፡፡

ምርጫው የተራዘመው ፊፋ በምርጫው ሒደት ላይ እየተነሱ ያሉ ቅሬታዎች ሳይፈቱና መግባባት ላይ ሳይደረስ ምርጫው እንዳይካሄድ ትዕዛዝ በማስተላለፉ መሆኑ ታውቋል፡፡

ካሁን ቀደም በአውሮፓውያን የገና በዓልና በምርጫው ላይ የሚሳተፉ ዕጩዎች ተሳትፎ ላይ በተነሳ ቅሬታ ምክንያት ምርጫው ስለተራዘመ ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወሳል፡፡

ከመርሕ ይልቅ መጯጯህን የመረጠው የፌዴሬሽኑ አስመራጭ ኮሚቴ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ታኅሣሥ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ሰመራ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን የቀጣይ አራት ዓመት አመራር ለመምረጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ የፌዴሬሽኑን የምርጫ ሒደትና የዕጩ ተወዳዳሪዎችን ግለ ታሪክ መርምሮ እንዲያቀርብ ኃላፊነት የተጣለበት አስመራጭ ኮሚቴው፣ የነቀፌታ አስተያየት ከሚሰነዘርበት አንዱ በመርሕ ከመመራት ይልቅ በቡድንተኝነት ትርምስ ውስጥ መገኘቱ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ምርጫው በተያዘለት ጊዜ ሰሌዳ ለመከናወኑ ጥርጣሬ ማሳደሩ አልቀረም፡፡

የግለሰቦች ፍላጎት የሚያምሰው የኢትዮጵያ እግር ኳስ

ፊፋ (ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር) ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባሳሰበው መሠረት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከመከናወኑ አስቀድሞ የአስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ ተደርጓል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አስመራጭ ኮሚቴውን ለመምረጥ ሐሙስ ኅዳር 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የአስመራጭ ኮሚቴውን ማንነትም ይፋ አድርጓል፡፡

የእግር ኳሱ ፖለቲካዊ ጡዘትና ዕጣ ፈንታው

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሥረኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 30 እና ኅዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አከናውኗል፡፡ ከስፖርታዊ ባህሪው ይልቅ ክልላዊ በሚመስል የፖለቲካ ጡዘት ለሁለት ቀን ትርጉም አልባ ውይይት አድርጎ መጠናቀቁ በተነገረለት በዚሁ ጉባዔ፣ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው የአስመራጭ ኮሚቴ ሳይሰየም መቅረቱ ሰሞነኛ ጉዳይ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡

‹‹የእግር ኳሱ ሥርዓትና አካሄድ ለብልጣ ብልጦችና ለሕገወጥ ደላሎች መበልፀጊያ የተመቸ ሆኗል››

አቶ አስናቀ ደምሴ፣ የአዲስ አበባ እግር ኳስ አሠልጣኞች ማኅበር የሕግ አገልግሎት ኃላፊ ይህ ወቅት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ በብዙ መልኩ ከአዎንታዊ ይልቅ አሉታዊ ጎኑ ጎልቶ የሚነገርበት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ)፣ በወርኃዊ የአገሮች የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ በከፍተኛ  ደረጃ ውጤቷ ማሽቆልቆሉ ይጠቀሳል፡፡