Skip to main content
x

የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትብብርና ውጥረት ውስጥ ያለችው የኢትዮጵያ ሚና

የአፍሪካ ኅብረት ከተቋቋመበት ጊዜ ቀደም ብለው በነበሩ ዓመታት ከቅኝ ግዛት ነፃ የወጡ የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ ትኩረት የነበረው፣ አኅጉራዊ ውህደትን ማምጣት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በወቅቱ ከኢኮኖሚያዊ ውህደትና ከፖለቲካ ውህደት የትኛው ይቅደም በሚለው አታካራ ወደ አንድ መምጣት አቅቷቸው፣ በጎራ በመከፋፈል ወደ ፉክክርና ክርክር ገብተው ነበር፡፡

በታሪካዊ ቀናቸው ዕውን የሆነው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኪነ ቅርፅ

በመጨረሻም ዕውን ሆነ፡፡ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (ቀኃሥ) ሐውልት በአፍሪካ ኅብረት ጠቅላይ ጽሕፈት ግቢ ቆመ፤ በታሪካዊቷ የካቲት 3 ቀን 2011 ዓ.ም.፡፡ ተፍጻሜተ ዘውዳዊ መንግሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በንጉሠ ነገሥትነት ከ1923 እስከ 1967 ዓ.ም. በወታደራዊ ደርግ እስከ ተገለበጡ ድረስ ኢትዮጵያን ገዝተዋል፡፡

 ለአፍሪካ ኅብረት በጀት የአባላቱን መዋጮ በሚጠይቀው ማዕቀፍ ኢትዮጵያ በዓመት እስከ 40 ሚሊዮን ዶላር ልታዋጣ ትችላለች

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሚተዳደርበትን የገንዘብ አቅምና በጀቱን በአባል አገሮች እንዲሸፈን ለማድረግ እያንዳንዱ አባል አገር በሕጋዊ የገቢ ንግዱ ላይ የ0.2 በመቶ ታክስ በመጣል መዋጮ እንዲያደርግ ስምምነት ከተደረሰ ሦስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት በአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ወቅት ይመረቃል

በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚቆመው የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሌሎች አገሮች መሪዎች በሚገኙበት ተመርቆ ይፋ እንደሚሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታወቁ፡፡

የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካውያን የመፍታት ጥረት ምን ያህል ይሳካል?

የአፍሪካውያንን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍና የእርስ በርስ መደጋገፍን መርህ በማድረግ የተመሠረተው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አአድ)፣ የተነሳለትን ዓላማ ብዙም ሳያሳካ ወደ ኅብረትነት መሸጋገሩን የሚገልጹ በርካታ ትንታኔዎች ይቀርባሉ፡፡

‹‹ኢትዮጵያዊነትን ከሰላም ጋር አንድ ለማድረግ መሥራት አለብን›› ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ወ/ሮ ዘውዲቱ ምኒልክን ንግሥተ ነገሥታት፣ ራስ ተፈሪ መኮንን ደግሞ ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ በማድረግ መስከረም 17 ቀን 1909 ዓ.ም የዳግማዊ አፄ ምኒልክን ዙፋን ካረካከበው ታሪካዊ ክስተት ወዲህ፣ ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዚዳንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሹመዋል፡፡

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት በጥር ወር ይጠናቀቃል

በአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ እየተገነባ የሚገኘው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሐውልት፣ ግንባታው በጥር 2011 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡ ሐውልቱ በዋናነት ንጉሡ ለአፍሪካ ኅብረት መቋቋም፣ እንዲሁም የአፍሪካ አገሮች በፀረ ቅኝ ግዛት ትግላቸው ወቅት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዕውቅና ለመስጠት ሲባል እንዲገነባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ድንበር የማይወስነው ጉዞ በአፍሪካ

በዓለም ላይ በድህነታቸው የሚታወቁት 75 በመቶ የሚሆኑ አገሮች መገኛቸው አፍሪካ ነው ይላል አንድ ሰነድ፡፡ ከድህነት ወለል በታች የሆኑ አሥሩ አገሮች ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሲሆን፣ ከጠቅላላ ሕዝባቸው 48 በመቶ የሚሆኑት በቀን 1.25 ዶላርና ከዚያ በታች ያገኛሉ፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለዚምባብዌ ምርጫ የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን እንዲመሩ ተመረጡ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚካሄደው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በታዛቢነት የሚገኘውን የአፍሪካን ኅብረት ኮሚሽን ቡድን እንዲመሩ ተመረጡ፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ አዲስ ምዕራፍ

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የጠቅላይ ሚኒትርነት ሥልጣኑን የተቀበሉት ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በበዓለ ሲመታቸው ላይ ካሰሙት አነቃቂ ንግግሮችና ሐሳቦች መካከል በዓብይነት ከተነሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ የኤርትራን ጉዳይ የተመለከተ ነበር፡፡