Skip to main content
x

በአዲስ አበባ ከተማ ፍጻሜ ጨዋታ 39 ተመልካቾች ለጉዳት ተዳርገዋል

ዘጠኙ ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ከፍተኛ ሆስፒታል አምርተዋል በ12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ በደጋፊዎች መካከል በተከሰተ አለመግባባት ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ተመልካቾች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. በቅዱስ ጊዮርጊስና በኢትዮጵያ ቡና  ክለቦች መካከል በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ የመጀመርያው አጋማሽ ከተጠናቀቀ በኋላ በተከሰተው የተመልካቾች እንካ ሰላንትያ በተፈጠረው ግብግብ በበርካታ ተመልካቾች ላይ ጉዳት በመድረሱ በተለያዩ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡