Skip to main content
x

በቅርስነት የተመዘገቡ ሕንፃዎች መፍረስ ቅሬታ አስነሳ

ሕንፃዎቹ እንዲፈርሱና እንዲታሸጉ ያዘዙት ኃላፊ ታስረው ተፈቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት በተለምዶ ካዛንችስ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ከ80 ዓመታት በፊት በፋሽስት ጣሊያን እንደታነፁና በቅርስነት እንደተመዘገቡ የተገለጹ ሕንፃዎች መፍረስ ቅሬታ አስነሳ፡፡  

የቤቶች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች የምደባና ደመወዝ አከፋፈል ሁኔታ አሳስቦናል አሉ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሠራተኞች ተቋሙ ከመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲነት ወደ ኮርፖሬሽን በመቀየሩን ምክንያት፣ ከከፍተኛ ኃላፊዎች ውጪ ላሉ ሠራተኞች ምደባ አለመካሄዱና ተሠርቷል በተባለው አዲስ መዋቅር መሠረት የደመወዝ ክፍያ አለመፈጸሙ እንዳሳሰባቸው ገለጹ፡፡

ቤቶች ኮርፖሬሽን ነባር ይዞታዎችን ለማስጠበቅ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ሊዋዋል ነው

በቅርቡ በ33.1 ቢሊዮን ብር ካፒታል በድጋሚ የተቋቋመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በመሀል ከተማ የሚገኙ ነባር ይዞታዎችን ለማስጠበቅ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር የስምምነት ሰነድ ሊፈራረም ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ በራሱ ይዞታ ሥር የሚገኙ ቪላ ቤቶችን በማፍረስ፣ ዘንድሮ ሦስት ሺሕ ቤቶችን ለመገንባት እየተዘጋጀ ነው፡፡