Skip to main content
x

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ኢንዶኔዥያ ውስጥ ተገዶ አረፈ

ሰኞ ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ሲንጋፖር ሲበር የነበረ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 777 ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን፣ የኢንዶኔዥያ የአየር ክልል ያለ በረራ ፈቃድ በመግባቱ በኢንዶኔዥያ አየር ኃይል ተገዶ እንዲያርፍ ተደረገ፡፡

ሲቪል አቪዬሽን የግሉን ዘርፍ ያበረታታል ያለውን ሕግ እያረቀቀ ነው

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የግሉ ዘርፍ በአቪዬሽን መስክ ኢንቨስት እንዲያደርግ የሚያበረታታ ሕግና ደንብ በማርቀቅ ላይ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ዓርብ ታኅሳስ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው የምክክር መድረክ ያዘጋጀውን ረቂቅ የሲቪል አቪዬሽን አዋጅ ማሻሻያ፣ የአየር ትራንስፖርት ተደራሽነትና ማስፋፊያ ደንብና የአነስተኛ ኤርፖርቶች ባለቤትነት፣ ግንባታና አስተዳደር ደንብ ለውይይት አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሌሎች አየር መንገዶች የአክሲዮን ድርሻ ሊሸጥ እንደሚችል ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአክሲዮን ድርሻ በከፊል በመሸጥ ወደ ግል የተወሰኑ ድርሻዎችን ለትልልቅ የአፍሪካ አየር መንገዶች ማስተላለፉ እንደማይቀር ይፋ አደረገ፡፡ በእንግሊዝ ሳምንታዊ በረራውን ወደ 11 ያሳደገበትን የማንቸስተር ከተማ መዳረሻ ይፋ አድርጓል፡፡

‹‹አየር መንገዱ የአገር አምባሳደርና የሁሉም ኢትዮጵያውያን ንብረት ነው›› አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራዕይ 2025 የዕድገት መርሐ ግብር ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ እ.ኤ.አ. 2011 ጀምሮ፣ በየዓመቱ ከ20 እስከ 30 በመቶ በማደግ ላይ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ አየር መንገድ የአገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ተሸክሞ የሚበር የአገር አምባሳደር ነው ብለዋል፡፡

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በ70 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ተጠረጠሩ

በቡድን በመደራጀትና የሌሎች ሠራተኞችን ፊርማ አመሳስሎ በመፈረምና የሥራ ዓድማ በማድረግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ኪሳራ አድርሰዋል ተብለው ተጠርጥረው የታሰሩ ዘጠኝ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች፣ በአየር መንገዱ ላይ የ70.9 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አድርሰዋል ተባለ፡፡

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እንደገና የተጠየቀባቸው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

አድማ በመፍጠር፣ በሕገወጥ መንገድ በመደራጀትና የሌሎች ሠራተኞችን ፊርማ አስመስለው በመፈረም የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንዲደርስበት አድርገዋል ተብለው ተጠርጥረው በታሰሩ ዘጠኝ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሠራተኞች ላይ እንደገና የተጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 6.87 ቢሊዮን ብር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 6.8 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ የድርጅቱን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም አስመልክቶ ዓርብ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ አየር መንገዱ 10.6 ሚሊዮን መንገደኞችና 400,339 ቶን ጭነት እንዳጓጓዘ ተናግረዋል፡፡