Skip to main content
x

ወደ ዓረብ አገሮች የሚሄዱ ሠራተኞችን ደመወዝ ለመወሰን የመዳረሻ አገሮች ምላሽ እየተጠበቀ ነው

የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅና ሕግን የተከተለ የሥራ ጉዞ እንዲደረግ ለአምስት ዓመታት ታግዶ የቆየውን የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት ጥቅምት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. የተጀመረ ቢሆንም፣ ወደ ዓረብ አገሮች የሚሄዱ የቤት ሠራተኞች ደመወዝ ምን ያህል መሆን እንደሚገባው መንግሥት ለቀጣሪ አገሮች ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ እየተጠባበቀ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

የአሠሪዎች ኮንፌደሬሽን በአሠሪውና በሠራተኛው አማካሪ ቦርድ ውስጥ ሕጋዊ ውክልና አገኘ

በቅርቡ የተመሠረተው የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን፣ በአሠሪና ሠራተኛ  ጉዳዮች ከፍተኛ ውሳኔ በሚሰጥባቸው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ እንዲሁም የፌዴራል የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ውስጥ በቋሚ አባልነት እንዲወክል የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መወሰኑ ታወቀ፡፡

በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የሚደረገው የቤት ሠራተኞች ቅጥር ስምምነት አዋጅ ፀደቀ

በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት መካከል የቤት ሠራተኞችን ቅጥር አስመልክቶ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የተደረገው ስምምነት ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ፀደቀ፡፡ በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ ከአራት ዓመታት በፊት ደርሶ በነበረው የሞት፣ አካል መጉደልና እንግልት ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚደረጉ ጉዞዎችን ማስቆሙ ይታወሳል፡፡

የአሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን እውቅና አገኘ

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ለተቋቋመው የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን የእውቅና የምስክር ወረቀት ሰጠ፡፡ በሚኒስትሯ ሒሩት ወልደ ማርያም (ዶ/ር) የተፈረመው የእውቅና የምስክር ወረቀት የተሰጠው ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ነው፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ በመሥራች ጉባዔው ፕሬዚዳንት፣ ሦስት ምክትል ፕሬዚዳንቶችንና ሌሎች ሰባት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጦ ነበር፡፡

ኤጀንሲዎች በሕገወጥ መንገድ ፈቃድ እንዲያገኙ ባደረጉ ሠራተኞች ላይ ዕርምጃ እንደሚወስዱ ሚኒስትሯ አስታወቁ

ከአራት ዓመታት በላይ ዕግድ ተጥሎበትና ሕጉ ጭምር ተቀይሮ መሥፈርቱን ለሚያሟሉ ለውጭ አገር ሥራና አሠሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች ሕጋዊ ፈቃድ መስጠት ሲገባቸው፣ መሥፈርቱን ላላሟሉ ኤጀንሲዎች ፈቃድ እንዲያገኙ ባደረጉት ሠራተኞች ላይ ዕርምጃ እንደሚወስዱ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሯ ሒሩት ወልደ ማርያም (ዶ/ር) ግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በሥራቸው ካሉ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ዳይሬክተሮችና ሌሎች የተለያዩ የክፍል ኃላፊ ሠራተኞች ጋር በመሆን፣ የውጭ አገር ሥራና አሠሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች ባለቤቶችና ወኪሎችን ማነጋገራቸው ታውቋል፡፡

ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ሄደው የሚሠሩባቸው የዓረብ አገሮች ተለዩ

ወደ ዓረብ አገሮች በብዛት እየሄዱ በቤት ሠራተኝነት በሚቀጠሩ ዜጎች ላይ በ2005 ዓ.ም. መጨረሻና 2006 ዓ.ም. መጀመርያ ላይ በደረሰ የሞት፣ ከባድ የአካል ጉዳትና እንግልት ሳቢያ መንግሥት ጥሎት የነበረውን የጉዞ ዕገዳ ከተነሳ በኋላ፣ በሕጋዊ መንገድ ሄደው መሥራት ለሚፈልጉ ዜጎች መንግሥት አገሮቹን ለይቶ አስታወቀ፡፡ መንግሥት የሁለትዮሽ ድርድርና ስምምነት የተፈራረመባቸው አገሮች ለጊዜው ኩዌት፣ ኳታርና ጆርዳን ብቻ በመሆናቸው ዜጎችም መሄድ የሚችሉት ወደነዚህ አገሮች ብቻ መሆኑ ታውቋል፡፡

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለ20 ኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ለመሠማራት ፈቃድ የሰጣቸው የአሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች 20 ብቻ ናቸው አለ፡፡ ይህ የተባለው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋናው አድማሱ፣ የሰው ኃይል ጥናትና ሥምሪት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አበበ ኃይሌና የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

ምንም እንኳን ለኤጀንሲነት ምዝገባ 923 ድርጅቶች ማመልከቻ ያስገቡ ቢሆንም፣ መሥፈርቱን አሟልተው ፈቃድ ማግኘት የቻሉት ግን 20 ብቻ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

መንግሥት በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ የጣለውን ዕገዳ አነሳ

መንግሥት ለዜጎች ደኅንነት በማሰብ በውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ ለዓመታት ጥሎት የነበረውን ዕገዳ ከማክሰኞ ጥር 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲነሳ ወሰነ። የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ዕገዳው እንዲነሳ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡ የሚታወቅ ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከጥር 22 ቀን ጀምሮ ዕገዳው እንዲነሳ መወሰኑን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የሚታየውን የሠራተኞች ብዝበዛ ያጣጣለው የዓለም ሠራተኞች ኮንፌደሬሽን ዝቅተኛ የደመወዝ ጣሪያ እንዲደነገግ ጠየቀ

ለሁለት ቀናት በተካሄደውና የአፍሪካ ሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲደነገግላቸው የጠየቀውን ፎረም ያዘጋጀው የዓለም ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን፣ በኢትዮጵያ የሚታየው የሠራተኞች ብዝበዛን ከመንቀፉም በላይ አገሪቱ ለሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚደነግግ ሥርዓት እንድትዘረጋ ጠየቀ፡፡ የዓለም የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ ሻረን ባሮው ከረቡዕ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የአፍሪካ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ፎረም ሲከፍቱ እንደጠየቁት፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ የወደፊቷ የጨርቃ ጨርቅ ማዕከል ስለመሆኗ ቢዘገብም፣ በሠራተኞች ረገድ ግን ብዝበዛ የሚፈጸምባት አገር እንደሆነች በምሳሌ አሳይተዋል፡፡

በአዲስ አበባ አብዛኞቹ አረጋውያን የምግብ እጥረት ይገጥማቸዋል

በአዲስ አበባ ከተማ 74 ከመቶ የሚሆኑት አረጋውያን ለከፍተኛ፣ እንዲሁም 97 ከመቶ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ መዳረሻ የምግብ እጥረት እንደሚገጥማቸው ተነገረ፡፡ ‹‹የመገናኛ ብዙኃን ትኩረት ለአረጋውያን›› በሚል ርዕስ ታኅሣሥ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጡረተኛና አረጋውያን ብሔራዊ ማኅበር ባካሄደው ዓውደ ጥናት ላይ  እንደተመለከተው፣ ለምግብ እጥረቱ የቤተሰብና የማኅበረሰብ ድጋፍ አናሳ መሆን እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡