Skip to main content
x

‹‹ሼክ አል አሙዲ ለኢትዮጵያ ልማትና ዕድገት አለኝታ ስለነበሩ እንዲፈቱ ጥረት አድርጌያለሁ››

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ባደረገው የፀረ ሙስና ዘመቻ ከአንድ ዓመት በላይ ታስረው የቆዩት ሼክ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ፣ ከእስር እንዲፈቱ የዓለም ጤና ድርጀት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) ሚና እንደነበራቸው ገለጹ፡፡

ከእስር ለመፈታት ከፍተኛ ገንዘብ መክፈላቸው የተሰማው ሼክ አል አሙዲ ሀብታቸው ማሽቆልቆሉ በፎርብስ ተረጋገጠ

እሑድ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ከአንድ ዓመት ከሁለት ወራት በላይ ታስረው የተለቀቁት ሼክ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ፣ ከእስር ነፃ ለመውጣት ከፍተኛ ገንዘብ መክፈላቸው ተሰማ፡፡ ባለፈው ዓመት 10.9 ቢሊዮን ዶላር ሀብት የነበራቸው ሼክ አል አሙዲ፣ በአሁኑ ወቅት በፎርብስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ላይ በ1.2 ቢሊዮን ዶላር ሀብት 159ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ፎርብስ እ.ኤ.አ. በ2018 ሼክ አል አሙዲ ከቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ማስወጣቱ ይታወሳል፡፡ በሰጠው ምክንያትም የትኛው ሀብት የእሳቸው እንደሆነ ግልጽነት ባለመኖሩ ነው ብሏል፡፡

መንግሥት ይፋ ያላደረጋቸው የኤርትራና የኢትዮጵያ ተደጋጋሚ ስምምነቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ባስቆጠሩዋቸው ስድስት ወራት ካከናወኑዋቸው ሥራዎች በዋናነት የሚጠቀሰው፣ ከኤርትራ ጋር የተደረገው ዕርቅ ነው፡፡ ይህ ዕርቅ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረውን የ20 ዓመታት የጦርነት ታሪክ በማብቃት የሰላም ምዕራፍ እንዲከፈት አድርጓል፡፡

ሀጅና ኢትዮጵያውያን ሀጃጆች

ከመሬት 909 ጫማ ከፍታ ላይ በምትገኘውና በሲራት ተራራ በተከበበች ምድረ በዳ መሬትን መኖሪያዬ ያለች አንዲት እናት ነበረች፡፡ እግር የሚፋጀውን አሸዋ፣ አናት የሚበሳውን ፀሐይ፣ ጨርቅ የሚያስጥለውን ሀሩርና በነፈሰ ቁጥር እየተጥመለመለ የሚነሳው አዋራ ተስፋ አስቆርጦ በረሃ እንዳይበላት የሚያበረታ አንድም ሰው አብሯት አልነበረም፡፡

በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የሚደረገው የቤት ሠራተኞች ቅጥር ስምምነት አዋጅ ፀደቀ

በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት መካከል የቤት ሠራተኞችን ቅጥር አስመልክቶ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የተደረገው ስምምነት ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ፀደቀ፡፡ በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ ከአራት ዓመታት በፊት ደርሶ በነበረው የሞት፣ አካል መጉደልና እንግልት ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚደረጉ ጉዞዎችን ማስቆሙ ይታወሳል፡፡

የአሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን ሼሕ አል አሙዲ እንዲፈቱ ሊጠይቅ ነው

የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን ሼሕ መሐመድ አሊ አል አሙዲ ከእስር እንዲፈቱ የሳዑዲን መንግሥት እንደሚጠይቅ አስታወቀ፡፡

ከአገሪቱ ግንባር ቀደም አሠሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ አል አሙዲ እንዲፈቱ ኮንፌዴሬሽኑ ብርቱ ፍላጎት ያለው በመሆኑ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከጀመሩት ጥረት ጎን ለጎን ኮንፌዴሬሽኑም የራሱን ጥረት ለማድረግ በመነሳሳት ላይ መሆኑን ኮንፌዴሬሽኑ ሐሙስ ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ገልጿል፡፡

ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ሠራተኞችን ለመላክ የሚያስችል የመጨረሻ ውይይት በፓርላማ ተደረገ

ሠራተኞችን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለመላክ በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት መካከል የሁለትዮሽ ስምምነት አስፈላጊ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን መላክ የሚቻልበትን ሁኔታዎችን በሚመለከት የመጨረሻ ውይይት ማክሰኞ  ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ተደረገ፡፡

ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ የተፈራረሙበት የሠራተኛ ቅጥር ስምምነት አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

የኢትዮጵያና የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት ከኢትዮጵያ በሚሄዱ የቤት ሠራተኞች ቅጥርና የሠራተኛና አሠሪ መብቶችን በተመለከተ ያደረጉት ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡ ስምምነቱ የሠራተኛና የአሠሪውን መብቶች፣ የሁለቱን አገሮች ሉዓላዊነት በጠበቀ መንገድ እንዲፈጸም የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ

መንግሥት ከፍተኛ የገንዘብና የእስራት ቅጣት የሚጥል ሕግ ያወጣ ቢሆንም፣ በተደራጀና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ሕጉን ተግባራዊ ሊያደርግ ባለመቻሉ በሕገወጥ ደላሎች የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ፡፡ ከአራት ዓመታት በፊት በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በቤት ሠራተኝነትና በሌሎች ሥራዎች ተሠማርተው በነበሩ ኢትጵያውያን ላይ በደረሰው ግድያ፣ አካል ማጉደልና ከፍተኛ እንግልት ምክንያት መንግሥት ዜጎች ወደ መካከለኛው ምሥራቃዊ አገሮች እንዳይጓዙ ዕግድ ጥሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሼክ አላሙዲን እንዲፈቱ መስማማታቸውን ገለጹ

ለጉብኝት ሳዑዲ ዓረቢያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የሚገኙት ሼክ መሐመድ አሊ አላሙዲን እንዲፈቱ ጠይቀው ስምምነት ላይ እንደደረሱ ተናገሩ፡፡