Skip to main content
x

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኛ በባልደረባቸው ተገደሉ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ክልል የቴክኒክ ኃላፊ በሽጉጥ ተገደሉ፡፡ ግድያው የተፈጸመው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ነው፡፡

ኃላፊው አቶ ይታያል  ካሳሁን የሚባሉ ሲሆን፣ ግድያውን ፈጽመዋል የተባሉት ተጠርጣሪ ደግሞ የአገልግሎቱ ቴክኒሻን (ሱፐርቫይዘር) የሆኑት አቶ ጌትነት ኃይሌ መሆናቸው ታውቋል፡፡

አቶ ጌትነት ከሟች ቢሮ ገብተው ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ከአቶ ይታያል ጋር ሲነጋገሩ እንደቆዩና ከቢሮው ፈጥነው በመውጣት እጃቸውን ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መስጠታቸው ታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ የመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት እንዲሠሩ የሚያደርግ ደንብ እየተዘጋጀ ነው

የአገሪቱ የመሠረተ ልማት ተቋማት በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂዱትን የዘፈቀደ ግንባታ እንዲያስቆም ኃላፊነት የተሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሠረተ ልማት ቅንጅት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የመሠረተ ልማት ተቋማቱን አቀናጅቶ የሚመራበትን ደንብ እያዘጋጀ መሆኑ ታወቀ፡፡