Skip to main content
x

ሥርዓተ አልበኝነት ይቁም!

አገር በለውጥ ማዕበል ውስጥ ሆና ወጣ ገባ የሚሉ ችግሮች ማጋጠማቸው ያለ ነው፡፡ ነገር ግን ሕገወጥነት ነግሦ ሥርዓተ አልበኝነት ሲሰፍን ደግሞ ቆም ብሎ ማሰብ ይገባል፡፡ መንግሥት ባለበት አገር ውስጥ ሕግ ማስከበር ካልተቻለ፣ ወዴት እየሄድን ነው በማለት አጥብቆ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡

ለአገር የሚበጀው በሕግ የበላይነት የሚተዳደር ሥርዓት መገንባት ነው!

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚከሰቱ ግጭቶች ሁሌም የሚጎዱት ንፁኃን ናቸው፡፡ የተለያዩ ዓላማዎችን ለማስፈጸም በደረሱ አደጋዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁኃን ሕይወታቸው ተቀጥፏል፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ለአካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ተዳርገዋል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከሚኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል፡፡

በንፁኃን ሕይወት የሚቆምሩ ለፍርድ ይቅረቡ!

መሰንበቻውን በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል እየተስተዋለ ያለው አሳዛኝ ድርጊት የአገር ህልውናን እየተፈታተነ ነው፡፡ በሶማሌ ክልል በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ ዘረፋና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ከባድ ጊዜ ውስጥ እንዳለን ያሳያል፡፡

ሕግና ሥርዓት ሲጠፋ አገር በረት ይሆናል!

በሕግና በሥርዓት የማይተዳደር አገር የሥርዓተ አልበኞች መፈንጫ ይሆናል፡፡ በተለይ አገር የፖለቲካ ሽግግር ውስጥ ስትሆን ሕግና ሥርዓት ካልኖረ ለትርምስ በር ይከፈታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ሥፍራዎች የሚሰሙት የግጭት፣ የሞትና የውድመት ዜናዎች እረፍት ይነሳሉ፡፡

በምሕረት አዋጁ አሳዛኙ የታሪክ ምዕራፍ ይዘጋ!

ዓርብ ሐምሌ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የምሕረት አዋጁን አፅድቋል፡፡ አዋጁ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ለተሳተፉ፣ የፖለቲካ መብታቸውን ለመጠቀም እንቅስቃሴ በማድረጋቸው መንግሥት ሲፈልጋቸው ከአገር ሸሽተው በተለያዩ አገሮች በስደት ለሚኖሩ ምሕረት ለመስጠት፣ በተጨማሪም የእርስ በርስ ጥላቻንና ጥርጣሬን በማስወገድ በብሔራዊ መግባባት አብሮ ለመሥራት ሲባል መውጣቱ ተገልጿል፡፡

የአገር ሸክም የሚቃለለው በተቋማት ግንባታ ነው!

የዘመናት የአገር ሸክምን ለማቃለል ሲባል መጠነ ሰፊ የሆነ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እየተገባ ነው፡፡ ይህ ለውጥ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ በማጠንጠን ኢትዮጵያን ከነበረችበት ቀውስ ውስጥ ለማውጣት ላይ ታች እየተባለ ነው፡፡

እያገረሹ ያሉ ግጭቶች መላ ይፈለግላቸው!

ለሦስት ዓመታት ያህል የዘለቀው ደም አፋሳሽ ግጭት በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ረገብ ቢልም፣ በተለያዩ ምክንያቶች የሚቀሰቀስ ግጭት ግን ገጽታውንና አድማሱን እያሰፋ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በፓርላማ ከተሰየሙበት ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ቢታይም፣ ከእግር ኳስ ሜዳዎች እስከ ክብረ በዓላት ሥነ ሥርዓቶች ድረስ ምክንያታቸው በውል ያልታወቀ ግጭቶች በብዙ ሥፍራዎች አጋጥመዋል፡፡

አገርን የማያስቀድም አጀንዳ እርባና የለውም!

የአገር ህልውና ለድርድር አይቀርብም፡፡ የአገር ሰላምና ደኅንነት መቼም ቢሆን ለፖለቲካ ሒሳብ ማወራረጃነት መዋል የለበትም፡፡ የአገር ጉዳይ ሲነሳ በቀጥታ የሚመለከተው ከ100 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያንን ነው፡፡ በአገሪቱ አራቱም ማዕዘናት ውስጥ የሚኖሩና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከአያት ከቅድመ አያቶቻቸው የወረሱት ጥልቅ የሆነ የአገር ፍቅርን ነው፡፡

ለብሔራዊ መግባባት የማይጠቅሙ አፍራሽ ድርጊቶች ይምከኑ!

ኢሕአዴግ የደርግ መንግሥትን በትጥቅ ትግል አስወግዶ ሥልጣን ከያዘ 27 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ እነዚህ 27 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ክስተቶችን አስተናግደዋል፡፡ ከአሀዳዊ ወደ ፌዴራላዊ ሥርዓት በመሸጋገር በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ መስኮች በርካታ ጉዳዮች ተከናውነዋል፡፡