Skip to main content
x

የግድቡ ወይዘሪት አምባሳደር

​​​​​​​በተለያዩ ዓለም አገሮች ለትውልድ የሚተርፉ አገራዊ ፋይዳቸው የጎላ ግንባታዎች ይከናወናሉ፡፡ ግንባታዎቹ በመሠረተ ልማት አውታርነት ለዜጎች ከሚሰጡት ቁሳዊ አገልግሎት ባሻገር ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው ታሪካዊ ቅርስ እስከመሆን ይደርሳሉ፡፡

የሳልሳ ሀሁ…

የአፍሪካ ሙዚቃና ባህል ልውውጥ ፌስቲቫል (አፍሪካ ሚውዚክ ኤንድ ካልቸራል ኤክስቼንጅ ፌስቲቫል)፣ የአፍሪካ ቀንን  ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የሙዚቃ ፌስቲቫል ሲሆን፣ ከወራት በፊት በግዮን ሆቴል ሲካሄድ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ ድምፃውያንን አሳትፏል፡፡ መርሐ ግብሩ በተካሄደበት ወቅት ከዘፋኞቹ ጎን ለጎን የታዳሚዎችን ቀልብ የሳቡት ባይላሞር በሚባል የዳንስ ትምህርት ቤት ውስጥ ከሚያስተምሩ መምህራን ጋር ይደንሱ የነበሩ ታዳጊዎች ናቸው፡፡

ሆሎካስትን በሰባት አገር ፊልሞች

አዲስ ቪዲዮ አርት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ውጤቶች የተካተቱበት ፌስቲቫል ሲሆን፣ በቅርቡ የፌስቲቫሉ ሁለተኛ ዙር ተካሂዷል፡፡ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በስደትና በሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የቪዲዮ ሥነ ጥበብ ውጤቶችም ቀርበዋል፡፡ ከነዚህ ሥራዎች መካከል፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚ ጀርመኑ አዶልፍ ሒትለር ወደ ስድስት ሚሊዮን አይሁዳውያንን ያስጨፈጨፈበትን ሆሎካስት በመባል የሚታወቀውን ወቅት የተመረኮዙ የቪዲዮ ሥራ ጥበቦች ይገኙበታል፡፡

የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች አበርክቶ

የሥነ ጽሑፍ ወዳጆች፣ ስለ ሥነ ጽሑፍ መርሐ ግብሮች ሲያስቡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ማስታወሳቸው አይቀርም፡፡ የሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል መገኛ የሆነው ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ባለው የባህል ማዕከል በርካታ የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች ተካሂደዋል፡፡ የበርካታ አንጋፋ ጸሐፍት መነሻም ማዕከሉ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ተማሪዎች ባሻገር የሌሎች ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችም የሥነ ጽሑፍ ምሽቶቹን በጉጉት ይጠባበቃሉ፡፡ ምሽቶቹ በርካታ የሥነ ጽሑፍ ውጤቶች የቀረቡባቸው እንዲሁም ዛሬ ላይ በሥነ ጽሑፍ ስመጥር የሆኑ ባለሙያዎች የወጡባቸውም ናቸው፡፡ እንደ ምሳሌ በዕውቀቱ ሥዩምን ማንሳት ይቻላል፡፡

ለ13 ዓመታት የአንበሳ አውቶቡስን አንበሳ የሣለችው  አርቲስት

‹‹ዘመን›› የተሰኘው የዓይናለም ገብረማርያም የሥዕል ዐውደ ርዕይ፣ የሠዓሊቷን የ40 ዓመታት ሥነ ጥበባዊ ጉዞ ያስቃኛል፡፡ በአዲስ አበባ ሙዚየም ከጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለ15 ቀናት ይታያል፡፡ ሠዓሊቷ እንደምትናገረው፣ በ1970ዎቹና 80ዎቹ በ90ዎቹም የሠራቻቸው ሥራዎች በምን ሒደት እንዳለፉ የምታሳይበት ዐውደ ርዕይ ነው፡፡ ‹‹የ40 ዓመታት ጉዞዬን ሕዝቡ እንዲያይ እፈልጋለሁ፡፡ በየወቅቱ ያለው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ማሳያም ነው፤›› ትላለች፡፡

የሞርጋን ቤተሰብ በልደት ዋዜማ

‹‹ሙዚቃ በየምንሔድበት አገር እናቀርባለን፡፡ ወደ ኢትዮጵያ በዚህ የበዓል ወቅት መምጣት ግን ሙዚቃ ከማቅረብም በላይ ነው፡፡ ለገና በዓል በኢትዮጵያ መገኘታችን ታላቅ ደስታ ሰጥቶናል፤›› በማለት ነበር የሞርጋን ሔሪቴጅ ባንድ ወንድማማቾች የተናገሩት፡፡ በልደት በዓል ዋዜማ በኤቪ ክለብ ሙዚቃዎቻቸውን ለማስደመጥ ከናይሮቢ፣ ኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡

የሠዓሊቷ ጉዞ በሦስቱ መንግሥታት

ከወራት በፊት፣ ሠዓሊት ደስታ ሐጎስ ስቱዲዮዋ ውስጥ ጋዋን ለብሳ፣ ሸራተን አዲስ በየዓመቱ ለሚያካሂደው ‹‹አርት ኦፍ ኢትዮጵያ›› ዐውደ ርዕይ አሥረኛ ዙር የሚሆን ሥዕል እያዘጋጀች ነበር፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልኳ ሲጠራ እጇ ላይ ያለውን ቀለም በጋዋኗ ጠርጋ አነሳች፡፡ የተደወለላት ከአምስት አሠርታት በላይ በሥነ ጥበቡ ላበረከተችው አስተዋፅኦ እውቅና እንደሚሰጣት ለመግለጽ ነበር፡፡ አንድ የሽልማት ድርጅት በሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ ዘርፍ የዕድሜ ዘመን የሥዕል የከፍተኛ ክብር ተሸላሚ መሆኗን የሚያበስር ደብዳቤም ላከላት፡፡

በታሪክ ነገራ ላይ ያተኮረው የፊልም ፌስቲቫል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር 12ኛውን የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል (ኢትዮ ፌስት) መክፈቻ ለማስተናገድ መዘጋጀቱን ከሩቅ የሚታዩት ባነሮች ይናገራሉ፡፡ ‹‹ሳንኮፋ፣ የታሪክ አተራረክ ጥበብ›› በሚል የሚከናወነውን ፌስቲቫል የሚያስተዋውቁ ፖስተሮች በብሔራዊ አካባቢ በሚገኙ ምሰሶዎች ላይም ተለጥፈዋል፡፡ ከታኅሣሥ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሰባት ቀናት የሚቆየው ፌስቲቫሉ በብሔራዊ ቴአትር የተከፈተው አመሻሽ ላይ ነበር፡፡

ሰሎሞን ዴሬሳ!

በቅርቡ በ80 ዓመቱ ዜና ዕረፍቱ የተሰማው፣ በዘርፈ ብዙ ዕውቀቱ ተጠቃሽ የነበረው ዕውቁ ገጣሚና ጸሐፊ፣ ጋዜጠኛና የፍልስፍና መምህር ሰሎሞን ዴሬሳ ሥርዓተ ቀብሩ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚኔሶታ ከተማ በግብአተ እሳት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ ነፍስ ኄር ሰሎሞን ዴሬሳ ከ19 ዓመታት በፊት (መስከረም 1991 ዓ.ም.) ከሪፖርተር መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር (በወቅቱ) ገዛኸኝ ጌታቸው ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ ነበር፡፡