Skip to main content
x

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታና ተሳትፎ መቀዛቀዙ ተገለጸ

የግንባታው የመሠረተ ድንጋይ ከተጣለ ስምንት ዓመታት ያስቆጠረው  የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታና ሕዝባዊ ተሳትፎ መቀዛቀዙ ተነገረ፡፡ ይኼ የተነገረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት፣ ከሚዲያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ለመወያየት ማክሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው፡፡

የሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች ሰጥተዋል በተባሉበት ሐሰተኛ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ክስ ላይ የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ

አሜሪካ ከሚገኘውና ታዋቂ ከሆነው ‹‹ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ›› ከሚባለው የትምህርት ተቋም ጋር ተቀራራቢ ስም ያለው ‹‹ካሊፎርኒያ ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ›› የሚል ሐሰተኛ የፈጠራ ተቋም ስም የተዘጋጀ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) እና ሦስተኛ ዲግሪ (ዶክትሬት) ሰጥተዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው የሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

በይግባኝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሄደው የአቶ ኤርሚያስ አመልጋ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የአክሰስ ሪል ስቴትና የዘመን ባንክ መሥራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የነፈጋቸውን የዋስትና ሕገ መንግሥታዊ መብት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለማስከበር ይግባኝ ያሉ ቢሆንም፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል፡፡

ከንግድ መርከቦች ግዥ ጋር በተያያዘ በሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች ላይ ብይን ተሰጠ

የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የግዥ መመርያን በመተላለፍ ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ ሁለት መርከቦችን በመግዛት፣ ከ544 ሚሊዮን ብር በላይ በሕዝብና በመንግሥት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ ክስ በመሠረተባቸው በእነ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው (14 ሰዎች) ላይ ብይን ተሰጠ፡፡

እነ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ ተደርጎ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

ከኢምፔሪያል ሆቴል ሽያጭ ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ጨምሮ 11 ተከሳሾች፣ አቅርበውት የነበረው የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደርጎ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ማክሰኞ የካቲት 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ሰጡ፡፡

ዓቃቤ ሕግ በኢምፔሪያልና በሪቬራ ሆቴሎች ላይ ባቀረበው ክስ ለቀረበበት መቃወሚያ ምላሽ ሰጠ

የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ በኮርፖሬሽኑ የተለያየ ኃላፊነት የነበራቸው ዘጠኝ ተከሳሾች፣ ከኢምፔሪያል ሆቴልና ከሪቬራ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤቶች ጋር በጥቅም በመመሳጠር ግዥ እንዲፈጸም ተደርጓል በሚል በቀረበው ክስ ላይ፣ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን መቃወሚያ በመቃወም ዓቃቤ ሕግ ምላሽ ሰጠ፡፡

በመንግሥት ላይ 71.6 ሚሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ የቀድሞ የሜቴክ ኃላፊዎች ተከሰሱ

በመንግሥት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመገልገልና በጥቅም በመመሳጠር፣ በመንግሥት ላይ ከ71.6 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ በሜቴክ ውስጥ የተለያዩ ኃላፊነት የነበራቸው ስድስት ሠራተኞችና አንድ ነጋዴ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሐሰተኛ ማስተርስና ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰጥ አድርገዋል መባላቸውን ተቃወሙ

‹‹ካሊፎርኒያ ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ›› ተብሎ ከሚጠራ ሐሰተኛ የፈጠራ ተቋም፣ ሐሰተኛ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ እንዲሰጥ አድርገዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ የክስ መቃወሚያቸውን ለፍርድ ቤት አቀረቡ፡፡

ከነጋዴ ጋር በመመሳጠር ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ የሜቴክ ኃላፊዎች ተከሰሱ

በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሥር የተቋቋመው ኅብረት ማኑፋክቸሪንግና ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ የነበሩ ኃላፊዎች ከአንድ ነጋዴ ጋር በመመሳጠር በፈጸሙት ሕገወት ግዥ፣ በሕዝብና በመንግሥት ላይ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ሰኞ ጥር 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

ከጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ጋር በተያያዘ 422 ሚሊዮን ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ የሜቴክ ኃላፊዎች ተከሰሱ

ለጣና በለስ ቁጥር አንድ ስኳር ማምረቻ ፋብሪካ የሚያገለግል የኃይል ማመንጫ (ፓወር ፕላንት) ግንባታ ግዥ ጋር በተያያዘ፣ ከ422 ሚሊዮን ብር ጉዳት በመንግሥት ላይ አድርሰዋል የተባሉ ሦስት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የተለያዩ የቀድሞ ኃላፊዎችና አንድ ቻይናዊ በሌለበት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡