Skip to main content
x

ኢትዮጵያ ለጂቡቲ የምትሰጠው ንፁህ ውኃ በሦስት ወራት ውስጥ እንደሚሠራጭ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ለጂቡቲ በነፃ የምትሰጠው የንፁህ ውኃ አቅርቦት ግንባታው ተጠናቆ፣ በሦስት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለጂቡቲያውያን መዳረስ እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ በጂቡቲ መንግሥት ወጪ የተካሄደው የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ አብዛኛው ሥራው ተጠናቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የጂቡቲ ከተሞች በመጠኑ የውኃ ሥርጭቱ መጀመሩም ተጠቅሷል፡፡

በአገሪቱ እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች የክልሎች አመራሮች ኃላፊነት ይወስዳሉ ተባለ

በአገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ላሉ ሕገወጥ ሠልፎችና ግጭቶች የክልሎች አመራሮች ኃላፊነት እንደሚወስዱ፣ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽሕፈት ቤት ኃላፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዓርብ ኅዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዳራሽ የተካሄደው የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤትና የክልል ደኅንነት ምክር ቤት ስብሰባ ሲጠናቀቅ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ የክልሎች አመራሮች እየተካሄዱ ያሉ ሕገወጥ ሠልፎችንና ግጭቶችን ማስቆም አለባቸው፡፡