Skip to main content
x

የመከላከያ ሠራዊቱ የሪፎርም ሥራዎች ክንውንና ውስጣዊ የፀጥታ ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ

የመከላከያ ሚኒስቴር በተቋሙና በሠራዊቱ ላይ ሁለንተናዊ የሪፎርም ሥራ እያከናወነ መሆኑን፣ ይኼንንም አስመልክቶ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ታኅሳስ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ሪፖርት አቅርቧል።

‹‹በውትድርና ዘመኔ በራስ ሕዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ ጥቃት ተፈጽሞ ያየሁት በምዕራብ ወለጋ ነው››

በአሁኑ ወቅት በምዕራብ ወለጋ የተፈጠረውን ፖለታካዊ መነሻ ያለው የፀጥታ ችግር በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተያየታቸውን የሰጡት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ፣ ‹‹በውትድርና ዘመኔ አይቼው የማለውቀው ጭካኔ፤›› ሲሉ ለፓርላማው ገለጹ።

የመከላከያ ሠራዊትን ሀብትና ንብረት ወደ ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓት የሚያስገባው አዋጅና አዳዲስ ድንጋጌዎቹ

መንግሥት በ2004 ዓ.ም. ከመደበው በጀት ውስጥ ከ6.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነውን ወጪና ገቢ ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉን፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር በ2005 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ይፋ ማድረጉ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሶ ነበር።

በመከላከያ ሠራዊት ሁለት አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ በነበሩት ጄኔራል አደም መሐመድ ቦታ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ መሾማቸውን የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ጄኔራል አደም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም፣ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያው የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን አስታውቀዋል፡፡

የፀጥታ አስከባሪዎች መጎዳታቸውንና የመሣሪያ መንጠቅ ድርጊቶች መታየታቸውን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ 17 የፀጥታ አስከባሪዎች መቁሰላቸውንና የተለያዩ ንብረቶች መውደማቸው ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሴክሬታርያት ኃላፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. አዋጁ ከታወጀ በኋላ የተከናወኑ ተግባራትን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

አቶ ሲራጅ አክለውም በተለያዩ አካባቢዎች የመሣሪያ ንጥቂያና የቀበሌ ጽሕፈት ቤቶችን ማቃጠል መፈጸሙን አስታውቀዋል፡፡ አንድ ፋብሪካ መቃጠሉንና አሥር የሕዝብ አውቶቡሶች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ

​​​​​​​ኢትዮጵያ በ2009 ዓ.ም. ለአሥር ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዜጎች ሰላማዊ ሠልፍ የማድረግ፣ የአገሪቱን ሰላምና ደኅንነት የሚያውኩ ጽሑፎችን የማተም፣ የማባዛት፣ የማሠራጨትና ሌሎች ክልከላዎች እንደነበሩ አይዘነጋም፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት የሚወስዳቸው ዕርምጃዎች ይፋ ተደረጉ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዓርብ የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ካወጀ በኋላ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት  የሚወስዳቸው አሥራ ስምንት ዕርምጃዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በሐዋሳ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገነባው የሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ውዝግብ አስነሳ

በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የሚገነባው የሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ፕሮጀክት የመሬት ይገባኛል ውዝግብ ተነሳበት፡፡ ሆቴሉ ሊገነባበት በታሰበበት ቦታ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ያነሳው የመከላከያ ሚኒስቴር መሆኑም ታውቋል፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር የሆነን ሆቴል በሐዋሳ ለመገንባት  የይሁንታ ደብዳቤ በከተማ አስተዳደሩ ተሰጥቶኛል የሚሉት ባለሀብቱ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው፣ ሆቴሉን ለማስገንባት ዲዛይን ለማሠራት ያደረጉት እንቅስቃሴ መደናቀፉን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹በታሪካችን በየትኛውም ጊዜ ዓይተነው የማናውቀው ተማሪ ሌላ ተማሪን የሚገድልበት ሁኔታ ተፈጥሯል››

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢሕአዴግ) ኢትዮጵያን መምራት ከጀመረ ከሃያ ስድስት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል፡፡ ፓርቲው አገሪቱን በመምራት ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ባስቆጠረበት ጊዜ ውስጥ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እየተከሰቱ ባሉ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችና ግጭቶች፣ የአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከመታወኩም በላይ የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፣ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡