Skip to main content
x

የዳንጎቴ ዕርዳታ ድርጅት በኢትዮጵያ ሥራ ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ

በኢትዮጵያ ከ700 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ ኢንቨስትመንት ያፈሰሱት ናይጄሪያዊው ቢሊየነሩ አላጂ አሊኮ ዳንጎቴ፣ የዕርዳታ ተቋማቸውን በኢትዮጵያ ሥራ የማስመጀር ሐሳብ እንዳላቸው የዳንጎቴ ፋውንዴሽን አስታወቀ፡፡

ከፖለቲካው ባልተናነሰ የኢኮኖሚው ጉዳይ ያሳስባል!

በአሁኑ ጊዜ ከአነስተኛ የንግድ ሥራዎች እስከ ትልልቅ ኢንቨስትመንቶች ድረስ ከፍተኛ የሆነ መቀዛቀዝ ይታይባቸዋል፡፡ አገር ጤና ሆኖ ውሎ ማደር ሲያቅተው እንኳን የተትረፈረፈ ምርት ይዞ ገበያ መውጣትም ሆነ መሸመት፣ በሰላም ወጥቶ መግባትም ያዳግታል፡፡ ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉና የኤክስፖርት ምርቶች  እንደ ልብ ገበያ ውስጥ ሳይቀርቡ፣ ከውጭ የሚገቡ መሠረታዊ አቅርቦቶችም እክል ሲገጥማቸው ሠርቶ አዳሪውንም ሆነ ሥራ ፈላጊውን ያስደነግጣል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞና መፃኢ ዕድሎች ለዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ታዳሚዎች ያስረዳሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የበርካታ አገሮች መሪዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ባለሀብቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት አመራሮች በሚታደሙበት የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም (መድረክ) ተገኝተው፣ በእሳቸው አመራር በኢትዮጵያ ስለተጀመረው የለውጥ ጉዞና መፃኢ ዕድሎች ረቡዕ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀትር በኃላ ያስረዳሉ።

በአመፅና በትጥቅ ጥቃት ሳቢያ በሞሮኮ ኩባንያዎች ላይ ለሚደርስ ጉዳት መንግሥት ካሳ ለመስጠት ግዴታ ሊገባ ነው

በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን በሚያፈሱ የሞሮኮ ኩባንያዎች ላይ ድንገተኛ በሆነ ሕዝባዊ አመፅ፣ የትጥቅ ጥቃት ወይም ተመሳሳይነት ባላቸው ክስተቶች ምክንያት ጉዳት ቢደርስ የጉዳት ካሳና መልሶ ማቋቋሚያ ክፍያን የሚያስገድድ ስምምነት መንግሥት ሊፈጽም ነው።

የቱርክ ኩባንያ በትግራይ ክልል በ750 ሚሊዮን ዩሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማውጣት ጀመረ

በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ቀጥተኛ መመርያ ተርኪሽ ሆልዲንግ ኤኤስ፣ በትግራይ ክልል በ750 ሚሊዮን ዩሮ አዲስ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት የኢንቨስትመንት ፈቃድ በማውጣት ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡

የሰው ኃይል ፍልሰት የኢንዱስትሪ ፓርኩን እየተፈታተነ ነው

በኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በመሥራት ላይ ያሉ የተለያዩ ኩባንያዎች፣ በሠራተኛ ፍልሰት እየተፈተኑ መሆኑ ታውቀ፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን ሰፊ የሰው ኃይል እንደ አንድ የኢንቨስትመንት ምቹ ዕድል ለመጠቀም ፓርኩ ከተቋቋመ እ.ኤ.አ ከ2008 ጀምሮ የገቡ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች፣ ሠራተኞቻቸው ሊቆዩላቸው ባለመቻላቸው ሥራቸው እየተስተጓጎለ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

በካፋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በተከሰቱ ግጭቶች በኢንቨስትመንቶች ላይ ጥቃት ደረሰ

በደቡብ ክልል በካፋ ዞን ገዋታና ዴቻ ወረዳዎች በተከሰቱ ግጭቶች በአካባቢው ባሉ ስምንት የእርሻ ኢንቨስትመንቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ በግጭቶቹም የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ተጎጂ ሆነዋል፡፡

በውጭ ኢንቨስትመንት መዳረሻነት ኢትዮጵያ ደረጃዋን እንዳሻሻለች የተመድ ሪፖርት አመለከተ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ ማክሰኞ ማምሻውን ይፋ ባደረገው ዓመታዊ የኢንቨስመንት ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ያስመዘገበችውን ከፍተኛ ውጤት አስጠብቃለች፡፡

በተመድ የዓለም ኢንቨስትመንት ሪፖርት መሠረት፣ ባለፈው ዓመት ወደ አፍሪካ ከመጣው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ የኢትዮጵያ ድርሻ 3.2 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ይህም ከአንጎላ፣ ከግብፅ፣ ከናይጄሪያና ከጋና በመከተል አምስተኛ ደረጃ በመያዝ ከፍተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት መዳረሻ እንደነበረች ይታወሳል፡፡

ኢንቨስተሮችን የሚያስደነግጡ ድርጊቶች በፍጥነት ይቁሙ!

ከሰሞኑ በዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅና በሁለት ሠራተኞች ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ለሦስት ዓመታት ያህል ከዘለቀው የፖለቲካ ቀውስ በማገገም አንፃራዊ መረጋጋት በተፈጠረላት በዚህ ወቅት ግድያው መጸፈሙ፣ አሁንም ለሥጋት የሚጋብዙ መፍትሔ ያልተገኘላቸው ችግሮች እንዳሉ ያመላክታል፡፡