Skip to main content
x

በሞጆ ከተማ በ100 ሚሊዮን ዶላር የቆዳ ኢንዱስትሪ ዞን ሊገነባ ነው

ከአዲስ አበባ ከተማ 76 ኪሎ ሜትር ርቀት በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ አቅራቢያ በ100 ሚሊዮን ዶላር የቆዳ ኢንዱስትሪ ዞን ሊገነባ ነው፡፡ ለአካባቢያዊ ብክለት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን የቆዳ ፋብሪካዎች አንድ ቦታ ለማሰባሰብ የታቀደው ከዓመታት በፊት ቢሆንም ዕቅዱ ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሠ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፕሮጀክቱ ጥናት ከሦስት ዓመት በፊት ቢጠናቀቅም ገንዘብ  ባለመገኘቱ ዘግይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በአነስተኛ ወለድ ብድር በመፍቀዱ ወደ ሥራ እየተገባ ነው ብለዋል፡፡

የቆዳና ሌጦ ግብይት ተጠሪነት ለእንስሳትና ዓሳ ሀብት ሚኒስቴር ሊዛወር ነው

ፀረ ሙስና ኮሚሽን አዲስ ኮሚሽነር ተሾመለት ሐሙስ ኅዳር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ለምክር ቤት የቀረበው የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፣ ተጠሪነቱ ለእንስሳትና ዓሳ ሀብት ሚኒስቴር እንዲሆን ሐሳብ አቀረበ፡፡ ለሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን አምስተኛ መደበኛ ስብሰባ ረቂቅ አዋጁን በንባብ ያቀረቡት የመንግሥት ምክትል ተጠሪው አቶ ጌታቸው በዳኔ እንደገለጹት፣ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት አዋጅ ምርቱ በየግለሰብ ቤቶች እየባከነ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ ይረዳል፡፡ በአምራቾች እጅ ስለሚቆይም የምርት ጥራት ችግርን እንዲያሻሽል ይረዳልም ብለዋል፡፡