Skip to main content
x

‹‹አትረሱም መቼም . . .››

የመጋቢት መባቻ ንጋቱ ጨለማ ሆኖ የተቀየረው ወደ ኬንያ መዲና ናይሮቢ ሲያመራ የነበረው የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ 8፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በደረሰበት አደጋ ባጭር መቀጨቱና ተሳፋሪዎቹን በኅልፈተ ሕይወት ማሰናበቱን ተከትሎ ነበር፣ ይህን የሐዘን እንጉርጉሮ ከነዜማው የግጥምና የዜማ ባለሙያው ሙሉ ገበየሁ የደረሰው፡፡

አደጋ በደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመረጃ ሳጥን ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ በደረሰበት ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን የመረጃ ሳጥን ላይ በፈረንሣይ ፓሪስ ምርመራ እየተካሄደ ነው፡፡ አደጋው በደረሰ ማግስት ሰኞ መጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም. አደጋው በደረሰበት ሥፍራ በተካሄደ ፍለጋ የተገኘውን የመረጃ ሳጥን ወስዶ ለመመርመር፣ የአሜሪካ ናሽናል ትራንስፖርት ሴፍቲ ቦርድና የእንግሊዝ ኤር አክሲደንት ኢንቬስትጌሽን ብራንች ቢጠይቁም፣ የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ባለሥልጣናት የመረጃ ሳጥኑን ወደ ፈረንሣይ ለመላክ ወስነዋል፡፡

እንደወጣ የቀረው የበረራ ቁጥር ኢቲ 302

እሑድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድና የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሠራኞች እንደ ወትሮ መደበኛ ሥራቸውን በማካሄድ ላይ ነበሩ፡፡ ገቢና ወጪ መንገደኞችን እንደተለመደው ሲያስተናግዱ ከፊታቸው የሚጠብቃቸውን ዱብ ዕዳ አያውቁም ነበር፡፡ ረፋዱ ላይ የደረሰው አስደንጋጭ ዜና ኤርፖርቱን በዋይታ ሞልቶታል፡፡

የአውሮፕላን አደጋው ምርመራ እስኪጠናቀቅ በትዕግሥት እንጠብቅ!

በመጀመርያ እሑድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 የበረራ ቁጥር ET 302 አውሮፕላን ላይ በደረሰው አስደንጋጭ አደጋ፣ ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን መፅናናትን እንደመኛለን፡፡

የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ ችግር እንደገጠመው ለበረራ ተቆጣጣሪዎች ማሳወቃቸው ተገለጸ

ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ ወደ ናይሮቢ ኬንያ ሲበር በቢሾፍቱና በሞጆ ከተሞች መካከል ኤጀሬ በምትባል ቦታ የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ ያሬድ ጌታቸው (ካፒቴን) ከቦሌ ኤርፖርት በተነሱ በደቂቃዎች ልዩነት ችግር እንደገጠማቸውና ተመልሰው ለማረፍ እንደሚፈልጉ ለበረራ ተቆጣጣሪዎች አስታውቀው እንደነበር ተገለጸ፡

ገንቢና ግንባታ አይተዋወቁም

በግንባታ ኢንዱስትሪው ውስጥ የሚታዩት ብልሹ አሠራሮች በብዙ መንገዶች ሲገለጹ ሰምተናል፡፡ በዓይናችን የምናያቸው ደረጃቸውን ያልጠበቁ ግንባታዎች ያስከፈሉትን የሕወይትና የሀብት ኪሳራ፣ ወደፊትም ሊያስከፍሉ የሚችሉት ጉዳት እንደዘበት አይታይም፡፡

የሰንሻይን ኮንስትራክሽን አደጋ የግንባታ ደኅንነት ጥያቄ አስነሳ

ቅዳሜ ታኅሳስ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ከሰንሻይን ኮንስትራክሽን ሕንፃ ላይ የወደቀ ሠራተኛ መሞቱ የግንባታ ደኅንነት ጥያቄዎችን በድጋሚ ቀሰቀሰ፡፡ አደጋው የደረሰው መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገነባ ትልቅ ሕንፃ ላይ ሲሆን፣ ሃያት ዲጀንሲ ሆቴል ከሚገነባበት አጠገብ መሆኑን ሪፖርተር በሥፍራው ተገኝቶ ታዝቧል፡፡

መለሰ አበራ የተባለ የ34 ዓመት ሠራተኛ በሕንፃው ላይ በሥራ ላይ በነበረበት ወቅት ወድቆ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ይህ በከተማይቱ ለግንባታ ደኅንነት የሚሰጠውን ትኩረት አናሳነት ያሳያል የሚሉ ተቃውሞዎች እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል፡፡ በቅርቡ ልጅ እንደተወለደ የተነገረው መለሰ ከሕንፃው እንደወደቀ ሕይወቱ አልፏል፡፡

በደቡብ ክልል በመሬት መንሸራተት የ23 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በደቡብ ክልላዊ መንግሥት ሁለት ዞኖች በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ሳቢያ መሬት በመንሸራተቱ የ23 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የክልሉ መንግሥት ማክሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፌዴራል መንግሥት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት፣ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከማምሻው ጀምሮ ከአካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎችን መላክ ጀምሯል፡፡

የትራፊክ አደጋ በሚበዛባቸው መስመሮች የአልኮል መመርመርያ መሣሪያ ሊሠራጭ ነው

የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመት ኤጀንሲ አደጋ በሚበዛባቸው አሥር ዋና ዋና መንገዶች፣ አልኮል ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን መቆጣጠር የሚያስችል መሣሪያ ጥቅም ላይ ሊያውል ነው፡፡ በፍጥነት ምክንያት ከሦስት ሰው በላይ ሕይወት የሚቀጥፉ አሥር መንገዶች በጥናት የተለዩ መሆናቸውን ኤጀንሲው ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡