Skip to main content
x

ገቢዎች ሚኒስቴር በአንድ ወር ውስጥ ተሰብስቦ የማያውቅ ገቢ ሰበሰብኩ አለ

የገቢዎች ሚኒስቴር በየካቲት ወር 2011 ዓ.ም. ብር 17.8 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ ከዕቅዱ 90 በመቶ በማሳካት በተቋሙ ታሪክ በአንድ ወር ውስጥ የተሰበሰበ ከፍተኛ የገቢ አፈጻጸም ማስመዝገቡን፣ ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዓርብ መጋቢት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የ18 ሚሊዮን ብር የሕንፃ ኪራይ ጥያቄ አስነሳ

በየካ ክፍለ ከተማ ሥር የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ ቀድሞ በዓመት አምስት ሚሊዮን ብር እየከፈለበት ካለው ሕንፃ በመልቀቅ በዓመት 18 ሚሊዮን ብር ወደሚከፈልበት ሕንፃ ለመዘዋወር የኪራይ ውል መፈጸሙ ጥያቄ ተነሳበት፡፡

ሪል ስቴት ኩባንያዎች ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ እንዲከፍሉ ተጠየቀ

በቅርቡ በከተማ ደረጃ የታክስ ንቅናቄ የጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ እንዲከፍሉ ጠየቀ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 130 የሪል ስቴት ኩባንያዎች የሚገኙ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባካሄደው ጥናት ስድስት ሪል ስቴት ኩባንያዎች ብቻ በአግባቡ የቤት ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ7,700 በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የግብር ዕዳ ምሕረት ማድረጉን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ የተጣለባቸው ግብር ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ እንዲታይላቸው ሲጠይቁ ለቆዩ 6,000 ነጋዴዎች፣ እንዲሁም በግብር ይግባኝ ተከራክረው ለተፈረደባቸው 1,780 ነጋዴዎችም ምሕረት እንዲደረግላቸው ካቢኔያቸው መወሰኑን አስታወቁ።

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በታክስ አሰባሰብ ተግዳሮት ገጥሞኛል አለ

በተያዘው በጀት ዓመት 34.5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ያቀደው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሁለት ዋና ጉዳዮች ተግዳሮት ገጠመው፡፡ የገቢዎች ቢሮ ተግዳሮት እየገጠመው የሚገኘው ከትክክለኛ ዋጋው ዝቅ አድርገው ደረሰኝ በሚቆርጡ (አንደር ኢንቮይስ)፣ እንዲሁም ደረሰኝ ቆርጠው ዕቃ ለመሸጥ ምንም ፍላጎት የሌላቸው ግብር ከፋዮች ነው፡፡

በሐሰተኛ ደረሰኝ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ፈጽመዋል የተባሉ 124 ድርጅቶች እየተመረመሩ ነው

በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ካቢኔ አባል ሆኖ የተዋቀረው የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ሕገወጥና ሐሰተኛ ደረሰኞችን ሲሸጡ የነበሩና በሐሰተኛ ሰነዶች ሲያጭበረብሩ የቆዩ 124 ድርጅቶችና ግለሰቦችን ዝርዝር ይፋ በማድረግ፣ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ሕገወጥ ግብይት በመፈጸማቸው የወንጀል ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኙ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን ከፍተኛ ግብር ተጥሎብናል ያሉ አገልግሎት ሰጪዎችን ጉዳይ ዳግም አያለሁ አለ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን በቀን ገቢ ግምት ላይ ተመሥርቶ በዝቅተኛ ግብር ከፋዮች ላይ የተጣለውን ከ90 በመቶ የታክስ ገቢ መሰብሰቡን ቢገልጽም፣ አገልግሎት በሚሰጡ ነጋዴዎች ላይ የተጣለው ታክስ ከአቅም በላይ መሆኑን የሚያመላክቱ መረጃዎችን በማግኘቱ በድጋሚ ለመመልከት መወሰኑን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን ወደ ከተማው ቢመለስም የግብር ከፋዮች ቅሬታ ቀጥሏል

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ከፌዴራል መንግሥት ተለይቶ እንዲመለስ ካስገደዱ ምክንያቶች መካከል የግብር ከፋዮች ቅሬታ ዋነኛው ቢሆንም፣ የግብር ከፋዮች ቅሬታ ግን አሁንም ጎልቶ እየተሰማ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን የአነስተኛ ግብር ከፋዮችን አብዛኛውን ቅሬታ መፍታቱን አስታወቀ

ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመውጣት እንደገና እንደ አዲስ እንዲደራጅ የተደረገው የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን፣ ባለፈው ዓመት ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳውና የቀን ገቢ ግምት ላይ ተመሥርቶ የሚሰላው ታክስ ላይ ሲነሱ የቆዩ ቅሬታዎች ላይ ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱን አስታውቋል፡፡