Skip to main content
x

መሰናዶን በዲጂታል ማስታወቂያ

ብሩክ ሰውነትና ሲራክ ኃይሉ በአዲስ አበባና በሌሎች አጎራባች ከተሞችም የሚካሄዱ ዝግጅቶችን ከሚከታተሉ መካከል ናቸው፡፡ የጥበብ፣ የቢዝነስ፣ የጤና አልያም ሌላ መርሐ ግብሮች ሲዘጋጁ ስለ ዝግጅቶቹ መረጃ ለመሰብሰብ ይሞክራሉ፡፡ ሆኖም በአዲስ አበባም ይሁን በሌሎች ከተሞች ዝግጅቶች ሲኖሩ በተዋቀረ መንገድ ለሕዝብ የሚደርሱበት መንገድ እምብዛም ስላልሆነ ይቸገራሉ፡፡ ችግሩ የሁለቱ ብቻ ሳይሆን የብዙዎች ነው፡፡