Skip to main content
x

የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ተቃጠለ

የጋምቤላ ከተማ መምህራን ሥራ አቁመው ነበር የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት፣ ቅዳሜ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ለእሑድ አጥቢያ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በተነሳ ቃጠሎ ወደመ፡፡ የክልሉ ፖሊስ የጠረጠራቸውን አሥር ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተገልጿል፡፡ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አከነ ኦፓዳ ለሪፖርተር እንደገለጹት በቃጠሎው ኮምፒዩተሮች፣ ሰነዶችና የቢሮ ዕቃዎች ወድመዋል፡፡ ከቃጠሎው ጋር በተገናኘ አሥር ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ቃላቸውን እየሰጡ ነው ብለዋል፡፡