Skip to main content
x

ካስቴል የዘቢዳርን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ያቀረበውን ዋጋ ባለአክሲዮኖች አልተስማሙበትም

የዥማር ኩባንያ ባለአክሲዮኖች በዘቢዳር ቢራ ያላቸውን የ40 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ለካስቴል ግሩፕ (ቢጂአይ ኢትዮጵያ) ለመሸጥ ወሰኑ፡፡ ካስቴል ግሩፕ አክሲዮኖቻቸውን ለመግዛት ያቀረበላቸውን ዋጋ ግን እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የዥማር ሁለገብ አክሲዮን ማኅበር አባላት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባካሄዱት ስብሰባ ወቅት፣ በዘቢዳር ቢራ ውስጥ ለያዙት የአክሲዮን ድርሻ የቀረበላቸው ዋጋ ከሚጠብቁት በታች በመሆኑ፣ የሽያጭ ዋጋው እንዲሻሻልና ለዚህም ቦርዱ ከካስቴል ግሩፕ ጋር እንዲደራደር ውክልና ሰጥተዋል፡፡

ዘቢዳር ቢራን ለመጠቅለል የተነሳው ካስትል ግሩፕ ግዥውን መቋጨት አልቻለም

በዘቢዳር ቢራ አክሲዮን ኩባንያ ውስጥ ዋነኛ ባለድርሻ የነበረውን የቤልጂየሙን የዩኒብራ ኩባንያን አክሲዮኖች ስለመግዛቱ ያስታወቀው ካስትል ግሩፕ፣ በኢትዮጵያውያን ባለድርሻነት የተያዙትን ቀሪዎቹን አክሲዮኖች ለመግዛት 1.3 ቢሊዮን ብር በማቅረብ ዘቢዳርን ለመጠቅለል እየተደራደረ ነው፡፡ አክሲዮኖቹን ለመግዛት ያቀረበው ዋጋ ግን ቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ ራያ ቢራን ለመግዛት ከሰጠው ዋጋ እንደሚያንስ ተሰምቷል፡፡

ካስቴል ግሩፕ የዘቢዳር ቢራን 58 በመቶ ድርሻ መግዛቱን ይፋ አደረገ

የፈረንሣዩ ካስቴል ግሩፕ የዘቢዳር ቢራ አክሲዮን ማኅበርን 58 በመቶ አክሲዮኖች መግዛቱን የሚያረጋግጥለትን ስምምነት መፈጸሙ ተገለጸ፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ተመሳሳይ የቢራ ፋብሪካዎችን የሚያስተዳድረው ካስቴል ግሩፕ፣ የዘቢዳር ቢራ ከፍተኛ ባለድርሻ የሚያደርገውን ግዥ መፈጸሙ ታውቋል፡፡

ዳሸን ባንክ ለቢጂአይ ኢትዮጵያ የ650 ሚሊዮን ብር ብድር ለቀቀ

ራያ ቢራን ለመግዛት የተስማማው ቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ ከዳሸን ባንክ የ650 ሚሊዮን ብር ብድር እንደተፈቀደለት ታወቀ፡፡ ሪፖርተር ከዳሸን ባንክ ምንጮች እንዳረጋገጠው ከሆነ፣ የብድር ጥያቄው በባንኩ ጸድቆ ክፍያው ለሚፈጸምላቸው የራያ ቢራ ባለአክሲዮኖች እንዲከፋፈል ታስቦ መለቀቁንም ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

አዋሽ ባንክ ለራያ ቢራ አክሲዮኖች ግዥ የሚውል 750 ሚሊዮን ብር ብድር ለቢጂአይ ፈቀደ

አዋሽ ባንክ ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለራያ ቢራ አክሲዮኖች ግዥ ለሚያውለው ክፍያ 750 ሚሊዮን ብር ብድር መፍቀዱ ታወቀ፡፡ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ አዋሽ ባንክ ለቢጂአይ ኢትዮጵያ የፈቀደው ብድር መጠን በአገሪቱ በግል ባንክ ለአንድ ፕሮጀክት በአንድ ጊዜ የተፈቀደ ከፍተኛው ነው፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በቅርቡ የራያ ቢራ አክሲዮኖችን ለመግዛት ላደረገው ስምምነት ክፍያ ለመፈጸም እንዲችል ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ባንኩ ብድሩን ፈቅዷል፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በራያ ቢራ ውስጥ ካለው የ42 በመቶ ድርሻው በተጨማሪ፣ ቀሪዎቹን አክሲዮኖች ለመግዛት ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

የቢራ ፋብሪካዎች በምርቶቻቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ አደረጉ

የቢራ ፋብሪካዎች በጠርሙስና በድራፍት ቢራ ምርቶቻቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ አደረጉ፡፡ ሰኞ ጥር 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ቢጂአይ ኢትዮጵያ የተጀመረው የዋጋ ጭማሪ፣ በተመሳሳይ ሌሎቹም የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ምርቶቻቸውን ማከፋፈል ጀምረዋል፡፡ ሁሉም የቢራ ፋብሪካዎች ያደረጉት የዋጋ ጭማሪ በተከታታይ ቀናት ተግባራዊ የሆነ ሲሆን፣ የዋጋ ጭማሪያቸውም ተመሳሳይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሰሞናዊው የዋጋ ጭማሪ መታዘብ እንደተቻለው የአንድ ሳጥን ቢራ በአዲስ አበባ የማከፋፈያ ዋጋ ከ214 ብር ወደ 251 ብር ከፍ ብሏል፡፡ የአንድ በርሜል የድራፍት የማከፋፈያ ዋጋ ከ600 ብር ወደ 700 ብር ከፍ ብሏል፡፡

ከምንዛሪ ለውጡ ሦስት ወራት በኋላ ቢራ አምራቾች የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ጀመሩ

ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተደንግጎ ተግባራዊ የተደረገው በ15 በመቶ የምንዛሪ ለውጡን በመንተራስ የዋጋ ጭማሪ ካደረጉ በርካታ የንግድ ዘርፎችና አምራቾች ውስጥ የቢራ ፋብሪካዎች ይጠቀሳሉ፡፡ የቢራ ፋብሪካዎች የምንዛሪ ለውጡን በመከተል ያደረጉት የምርት መሸጫ ዋጋ ጭማሪ አግባብ እንዳልሆነ ተነግሯቸውና ሕዝብም እንዲያውቀው ተደርጎ፣ የብር የዋጋ ጭማሪውን በማንሳት እንደ ቀድሟቸው በነባሩ ዋጋ እንዲያመርቱ በመንግሥት መገደዳቸው ይታወሳል፡፡

የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ ነው

የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በምርቶቹ ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርጎ ማከፋፈል መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ቢራ ፋብሪካዎች ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በማከፋፈያ ዋጋቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ ቢጂአይ ግን ይህንን የዋጋ ጭማሪ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

ቢጂአይ የዘቢዳር ቢራን ዋነኛ ባለድርሻ አክሲዮኖች መግዛቱን አስታወቀ

በኢትዮጵያ የቢራ ኢንዱስትሪ ከፍተኛውን የገበያ ድርሻ የያዘው ቢጂአይ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኩባንያ የሆነው ካስል ግሩፕ፣ የዘቢዳር ቢራ ዋነኛ ባለድርሻ የሆነውን ዩኒቢራ 60 በመቶ አክሲዮኖችን መግዛቱን አስታወቀ፡፡ በዘቢዳር ቢራ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነውን የአክሲዮን ድርሻ የያዘው የቤልጅየሙ ዩኒቢራ፣ አክሲዮኖቹን ሙሉ በሙሉ ለማስተላለፍ የሚያስችለውን ስምምነት ከካስል ግሩፕ ጋር ተፈራርሟል፡፡

ራያ ቢራ ከአክሲዮን ዝውውር እንዲከፍል የተጠየቀውን ታክስ በመቃወም ለመንግሥት አቤቱታ አቀረበ

ቢጂአይ ኢትዮጵያ የራያ ቢራን አክሲዮን ማኅበር ጠቅልሎ ለመግዛት ያቀረበውን ጥያቄ የተቀበሉ ባለአክሲዮኖች፣ የአክሲዮን ዝውውሩ ሕጋዊ ሒደት በአክሲዮን ማኅበሩ ቦርድ በኩል እንዲፈጸም ውክልና ሰጡ፡፡ ከአክሲዮን ዝውውሩ ጋር በተያያዘ ለመንግሥት የሚከፈለው የ30 በመቶ ታክስ ውዝግብ መፍጠሩ ተጠቆመ፡፡