Skip to main content
x

ለህዳሴ ግድቡ ግንባታ 98.7 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉ ተገለጸ

የዛሬ ሰባት ዓመት ገደማ ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የፕሮጀክትና የፋይናንስ አስተዳደር፣ እንዲሁም ወለድና የእርጅና ወጪ ጨምሮ በአጠቃላይ 98.7 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ተናገሩ።

የውኃ ሀብት ሚኒስቴር የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክት በፋይናንስ እጥረት መስተጓጉሉን አመነ

የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለማቅረብ ዓርብ ታኅሳስ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኙት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) የኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በፋይናንስ እጥረት ምክንያት መስተጓጎሉን አመኑ፡፡

የህዳሴ ግድቡን በአራት ዓመታት ለማጠናቀቅ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ መንግሥት ይፋ አደርጋለሁ አለ

በ2003 ዓ.ም. በይፋ ግንባታው የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአምስት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ የተመደበለት 80 ቢሊዮን ብር በጀት ቢሆንም፣ በተባለው ጊዜ ሳይጠናቀቅ ከመዘግየቱም በተጨማሪ ከተመደበለት በላይ ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ መፍጀቱን መንግሥት አስታውቋል፡፡

የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክት የገንዘብ እጥረት ገጠመው

በኦሞ ወንዝ ላይ የተጀመረው የኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ግንባታው መስተጓጎሉ ተሰማ፡፡ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ቀጥሎ በኢትዮጵያ ትልቁ የሆነው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ ከጅምሩ የፋይናንስ ግኝቱ ችግር እንዳለበት ሲገለጽ የቆየ ቢሆንም፣ የፋይናንስ እጥረቱ ሥር እየሰደደ መጥቶ ሠራተኞችን መቀነስ ተጀምሯል፡፡

አወዛጋቢው የረጲ ኃይል ማመንጫ ‹‹ቆሻሻ ከማቃጠል የዘለለ ሚና የለውም›› ሲሉ የውጭ ባለሙያ አጣጣሉ

ሥራ በጀመረ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንዲያቆም የተደረገውና ሦስት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ የፈሰሰበት የረጲ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ ቆሻሻ ከማቃጠል የዘለለ ሚና የለውም ሲሉ የዘርፉ የውጭ ባለሙያ አጣጣሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሀብቱን ግምት ለማወቅ ስምምነት ተፈራረመ

በማያቋርጡ ግዙፍ ግንባታዎች ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ያለውን ቋሚ ንብረትና የሀብት ምጣኔውን ለማወቅ የሚያስችል ጥናት እንዲያካሂድለት ከፌር ፋክስ አፍሪካ ፈንድ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

በዝቅተኛው እርከን እስከ 30 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ የተደረገበት የኤሌክትሪክ  ኃይል አቅርቦት በመጪው ወር ተግባራዊ ሊደረግ ነው

ከታኅሳስ 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለመጪዎቹ አራት ዓመታት ተግባራዊ እንደሚሆን የሚጠበቀው አዲሱ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የዋጋ ታሪፍ፣ በዝቅተኛው ደረጃ እስከ 30 በመቶ ጭማሪ ተደርጎበት መዘጋጀቱ ታወቀ፡፡

የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ በ6.5 ቢሊዮን ዶላር የሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ

በገንዘብ ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የሚመራው የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ፣ በ6.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገነቡ የሚታሰቡ 17 ሜጋ ፕሮጀክቶችን ይፋ አደረገ፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችና የፍጥነት መንገዶች ቅድሚያውን ወስደዋል፡፡

ለተጓተተው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ብድር እንዲፋጠን ተጠየቀ

ለኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ፕሮጀክት የሚያስፈልገው የኃይድሮና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ግዥ መዘግየት አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ በመሆኑ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ከቻይና መንግሥት ጋር በመነጋገር በፍጥነት የኮንሴሽናል ብድር እንዲያመቻች ተጠየቀ፡፡

ከተመረቀ ወር ያልሞላው ረጲ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራ አቆመ

በቅርቡ ሥራ የጀመረው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ በተመረቀ በሁለት ሳምንቱ ሥራ አቆመ፡፡ የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ 2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ወጥቶበት፣ ሥራ መጀመር ከነበረበት ጊዜ በሁለት ዓመት ዘግይቶ ነበር የተጠናቀቀው፡፡