Skip to main content
x

የኤርትራ ወደቦችን ለመጠቀም ዝግጅት መደረጉ ተመለከተ

ከሁለት አሥርት ዓመታት በኋላ የኤርትራ ወደቦችን እንደ አዲስ ለመጠቀም እየተካሄደ ባለው ዝግጅት፣ አገራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ዕቅድ መዘጋጀቱ ተመለከተ፡፡ የኤርትራ ወደቦች የሆኑትን አሰብና ምፅዋ ለመጠቀም የሚያስችል ዝግጅት እንዲያካሂድ ኃላፊነት የተሰጠው፣ ከዘርፍ መሥሪያ ቤቶች የተውጣጣ የቴክኒክ ኮሚቴና በከፍተኛ ባለሥልጣናት የተቋቋመው ዓብይ ኮሚቴ በቂ ዝግጅት ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የንግድ ሎጂስቲክስና የተወዳዳሪነት ችግሮችን እንደሚቀርፍ የሚጠበቀው ስምምነት

በኢትዮጵያ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የሚታዩ የሎጂስቲክስና የትራንስፖርት ወጪዎችን ጨምሮ የንግድ ዘርፉን ብሎም የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት ለማሻሻል በኢትዮጵያ መንግሥንትና ትሬድማርክ ኢስት አፍሪካ በተሰኘ ኩባንያ መካከል ስምምንት ተፈርሟል፡፡

በመንገዶች ባለሥልጣንና በትራንስፖርት ሚኒስቴር አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ሀብታሙ ተገኝ (ኢንጂነር) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አርዓያ ግርማይ ደግሞ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸው ታውቋል፡፡

ለአቶ ሀብታሙ የተጻፈላቸው ደብዳቤ ከሐሙስ ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲሱ የኃላፊነት ቦታ እንዲያገግሉ የሚረጋግጥ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የውጭና የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የተሳተፉበት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዓውደ ርዕይ ተካሄደ

በየዓመቱ የሚዘጋጀው ሁለተኛው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዓለም አቀፍ ዓውደ ርዕይ ከዓርብ፣ ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለሁለተኛ ጊዜ መካሄድ ጀምሯል፡፡ ከ60 በላይ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል፡፡  

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ አቀረቡ

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ለረዥም ዓመታት ሲያገኙዋቸው የነበሩ የሙያ ዕውቅና፣ የደመወዝና የተለያዩ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ምላሽ ያገኙ ዘንድ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የአቤቱታ ደብዳቤ አስገቡ፡፡ ጥያቄያቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ካላገኘ ከሥራቸው እንደሚለቁ አስጠንቅቀዋል፡፡

የኢትዮ ጂቡቲ ኮሪደር መንገድ በመበላሸቱ የተሽከርካሪዎች ምልልስ እየተስተጓጎለ ነው

ከሌሎች ጎረቤት አገሮች አንፃር ሲታይ ለመሀል ኢትዮጵያ ቅርብ የሆነው የጂቡቲ ወደብ ቢሆንም፣ በተለይ ከወደቡ እስከ ጋላፊ ድረስ ያለው 200 ኪሎ ሜትር መንገድ በመበላሸቱ፣ የተሽከርካሪዎችን ምልልስ ከማስተጓጎሉም በላይ፣ ለአላስፈላጊ የመለዋወጫ ዕቃዎች ወጪ እያደረጋቸው መሆኑን ባለንብረቶች አስታወቁ፡፡

የአገሪቱን የገቢ ዕቃዎች እንደታቀደው ማስገባት አልተቻለም ተባለ

የአገሪቱን የዘጠኝ ወራት የትራንስፖርት ጉዳዮች የተመለከቱ አፈጻጸሞችን ለሕዝብ ክንፍ በማስመደጥ ውይይት ያደረገው የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ካቀረባቸው ጉዳዮች አንዱ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችና ጭነቶችን የተመለከተው ይገኝበታል፡፡

የግል አቪዬሽን ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎቻቸው የአሥር ሚሊዮን ዶላር መድን እንዲገቡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

የዘጠኝ ወራት የዘርፉን አፈጻጸም ለመምከር የትራንስፖርት ሚኒስቴር በጠራው ስብሰባ ላይ የግል አቪዬሽን ኦፕሬተሮች ያደረባቸውን ቅሬታ አሰሙ፡፡ አውሮፕላኖች በሚንቀሳቀሱበት ወይም በምድረ አየር ክልል (በበረራ መነሻና ማረፊያ) ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች፣ የአሥር ሚሊዮን ዶላር የመድን ሽፋን ግቡ መባላቸውን ተቃውመዋል፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታዎች በቀረበው ቅሬታ ላይ እንደሚነጋገሩበት አስታውቀዋል፡፡

ሶማሊያ ቅሬታዋን ኢትዮጵያ ማስተባበያዋን ያስተጋቡበት የበርበራ ወደብ የዓረብ ሊግ እንዲገባበት ጥሪ ቀረበ

የግዛቴ አካል ከሆነውና ራሱን ነፃ መንግሥት ብሎ ከሚጠራ አካል ጋር የተደረገ ስምምነት ሉዓላዊነቴን ተጋፍቷል በማለት ቅሬታውን ያሰማው የሶማሊያ መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ከዱባዩ ዲፒ ወርልድ ኩባንያና ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የበርበራ ወደብ የባለድርሻነት ስምምነት ውድቅ እንዲደረግ ለዓረብ ሊግ ጥሪ አቀረበ፡፡