Skip to main content
x

የሞሮኮ ግዙፍ ኩባንያ በተፈጠሩ በርካታ ችግሮች የተዘጉ አምስት የማዳበሪያ ፋብሪካዎችን ይረከባል

በገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየኖች ከ250 ሚሊዮን ብር ወጪ ተገንብተው በተለያዩ ምክንያቶች ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ የማዳበሪያ ፋብሪካዎችን፣ የሞሮኮ ግዙፍ ኩባንያ ኦሲፒ በሊዝ ሊረከባቸው ነው፡፡

ለሜካናይዜሽን እርሻ የታጩት የአርሲ ባሌ ወጣቶች

የግብርናው ዘርፍ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋልታ ቢሆንም፣ ከዘመናዊ አሠራሮችና የአመራረት ስልቶች ጋር ያለው ቁርኝት ብዙ ይቀረዋል፡፡ ለዘመናት የዘለቀው የኢትዮጵያ ግብርና፣ ዛሬም በጥማድ በሬ፣ ይህም ካልተገኘ ፈረስና ሌላም የጋማ ከብት ሲብስም አራሹ ራሱን ከእንስሳቱ ጋር በማጣመር ሞፈርና ቀንበር እየጎተተ የሚያርስ ገበሬና ሁዳድ የበዛበት ግብርና ነው፡፡

የተምች ወረርሽኝ በዚህ ዓመት ከፍተኛ አደጋ መደቀኑ ተገለጸ

ምንጩ ከወደ ፓስፊክ አገሮች፣ ማዕከላዊ አሜሪካ ከመሆኑም በላይ የአሜሪካ የፀደይ ወራት ስያሜ በመያዝና በዩኤስ አሜሪካም ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ የሚጠቀስለትና ‹‹ፎል አርሚዎርም›› በመባል የሚጠራው የተምች ወረርሽኝ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገሮችን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አዳርሶ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም  ካለፈው ዓመት የበለጠ ጥፋት በኢትዮጵያ ሊያስከትል እንደሚችል ተገምቷል፡፡ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩኤስአይዲ) አማካይነት በሚመራው ፊድ ዘ ፊውቸር የኢትዮጵያ እሴት ሰንሰለት ፕሮግራም ቺፍ ኦፍ ስታፍ ኢያን ቼስተርማን ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ ወቅት እንዳስታወቁት፣ የተምች ወረርሽኙ የአገሪቱን ሰብሎች በመላመዱና የአየሩ ጠባይ ለመራባት ምቹ ስለሆነለት በዚህ ዓመት ሊያደርስ የሚችለው ጥፋት ካለፈው ዓመት ይልቅ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

ለአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ምርቶች የሚቀርቡበት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጀ

በአራት ክልሎች በ5.7 ቢሊዮን ብር እየተገነቡ ለሚገኙት አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግብርና ምርቶች ማቅረብ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጀ፡፡ በእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር፣ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስቴር፣ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀውን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በቆሎ ወደ ውጭ ኤክስፖርት እንዲደረግ የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

በተያዘው የ2009/2010 ምርት ዘመን ትርፍ በቆሎ በመመረቱ፣ ወደ ውጭ ኤክስፖርት ለማድረግ የመንግሥት ፈቃድ እየተጠበቀ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ፡፡በ2008/2009 ዓ.ም. በተወሰነ ደረጃ ትርፍ በቆሎ ተገኝቶ ስለነበር 620 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ወደ ጎረቤት ኬንያ መላኩ ይታወቃል፡፡ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ ኢያሱ አብርሃ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በተያዘው ምርት ዘመን በርካታ በቆሎ በመመረቱ ለመንግሥት ውሳኔ አቅርበዋል፡፡

ግብርናን ከበሬ ጫንቃ የማላቀቅ ፈተና

በመንግሥት በእርሻ ሥራ የታወቁ አካባቢዎች ከተለመደው አሠራር ወጥተው በግብርና ሜካናይዜሽን መጠቀም እንዲጀምሩ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል፡፡ የመንግሥት ዓይን ካረፈባቸው 32 የግብርና ሥነ ምኅዳራዊ አካባቢዎች ውስጥም ማኛ ጤፍ አምራቹ ጎጃም ይገኝበታል፡፡