Skip to main content
x

አምስት ነባር መንደሮችን ለማፍረስ ከተነሺዎች ጋር ውይይት ሊጀመር ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 78 ሔክታር መሬት ላይ ያረፉ አምስት ነባር መንደሮችን ለማፍረስ፣ ከተነሺዎች ጋር ውይይት ለመጀመር እየተዘጋጀ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሥር የሚገኘው የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ፣ ቀደም ብለው ከተካሄዱ የመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች በተሻለ የተነሺዎችን መብት እንደሚያስከብር አስታውቋል፡፡ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ግርማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት ኤጀንሲው ሙሉ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ በመሆኑ በቅርቡ ከተነሺዎች ጋር ውይይት ማድረግ ይጀምራል፡፡

የተቋረጠው መልሶ ማልማት 78 ሔክታር ላይ ያረፉ አምስት ነባር መንደሮችን በማፍረስ ሊጀመር ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነዋሪዎች በተደጋጋሚ በቀረበ ቅሬታ ምክንያት፣ በጊዜያዊነት ለሁለት ዓመታት ያቋረጠውን የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ በድጋሚ ለመጀመር ተዘጋጀ፡፡ በዚህም መሠረት 78 ሔክታር መሬት ላይ ያረፉ አምስት ነባር መንደሮች ይፈርሳሉ፡፡