Skip to main content
x

ግጭት በተቀሰቀሰባቸው ሥፍራዎች በወታደራዊ ዕርምጃዎች ብቻ መፍታት ውጤቱ የከፋ እንደሚሆን ተገለጸ

የአገር መከላከያ ሠራዊት አዛዥ መኰንኖች አገራዊ የፀጥታ ሁኔታና የመከላከያ ሪፎርም ሥራዎችን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ፣ መከላከያ ፀጥታን ለማስከበር ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሲገባ በቶሎ ግጭቶች የሚረግቡ ቢሆንም፣ በአንዳንድ አካባቢዎች በቶሎ የማይረግቡ ግጭቶች የመኖራቸው ምክንያት፣ የፀጥታ ማስከበሩ ሥራ ሙሉ በሙሉ ወታደራዊ ብቻ ባለመሆኑ ነው ሲሉ አስታወቁ፡፡

በአማራ ክልል በተፈጠረው ግጭት ላይ ምክክር ተደረገ

በአማራ ክልል በተለይም በምዕራብ ጎንደር ዞን የቅማንት ብሔረሰብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች የተከሰተውንና ከ50 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ሞትና ለበርካቶች መፈናቀልና ለንብረት ውድመት ምክንያት በሆነው ግጭት ሳቢያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተገኙበት በጎንደር ከተማ ዓርብ ታኅሳስ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ምክክር ተካሄደ፡፡

ከነትጥቃቸው ቤተ መንግሥት የገቡ ኮማንዶዎች በጽኑ እስራት ተቀጡ

መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ግዳጃቸውን አጠናቅቀው በመመለስ ላይ የነበሩና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥያቄ እናቅርብ በማለት ቤተ መንግሥት ከገቡ የመከላከያ ኮማንዶ አባላት በ66ቱ ላይ ከአምስት ዓመት እስከ 14 ዓመት የሚደርስ ቅጣት ተላለፈ፡፡ በቀሪዎቹ ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

ከነትጥቃቸው ቤተ መንግሥት ከገቡ ኮማንዶዎች 66ቱ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ተፈረደባቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ለማግኘትና ጥያቄዎችን ለመጠየቅ በሚል ምክንያት ከነትጥቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ገብተው ከነበሩ 216 የመከላከያ ሠራዊት መካከል 66ቱ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ፍርድ እንደተሰጣቸው ተገለጸ፡፡

የመከላከያ ሠራዊት ግጭት የተቀሰቀሰባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካባቢዎች ተሰማራ

ሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ውጥረትና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን፣ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው መሰማራቱ ታወቀ።

የባህር ኃይል በኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል ውስጥ መደበኛ ሠራዊት ሆኖ እንዲደራጅ ረቂቅ ሕግ ቀረበ

በአገር መከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ከምድርና ከአየር ኃይል በተጨማሪ፣ የባህር ኃይልና የልዩ ዘመቻ ኃይል መደበኛ የሠራዊቱ ኃይሎች ሆነው እንዲደራጁ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

‹‹ኢትዮጵያ የምትባል አገር ያለችው መከላከያ ውስጥ ነው››

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሙስ ጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ጋር የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቀው ጎንደር ሲደርሱ፣ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ውይይት አድርገው ነበር፡፡ በዚህ ውይይታቸው ወቅት ከቀረበላቸው ጥያቄ አንዱ በመከላከያ ውስጥ የአንድ ብሔር የበላይነት ስላለ እንዴት ይታረቅ የሚል ነበር፡፡

ያልተፈታው የቀድሞ ሠራዊት ጥያቄ

የቀድሞ የምድር ጦር ሠራዊት አመሠራረትና ታሪካዊ አመጣጥ ረዥም ዓመት ቢያስቆጥርም፣ በዘመናዊ ሠራዊትነት መደራጀት የጀመረው በ1927 ዓ.ም. ነው፡፡ በዚህ መልክ ከተደራጀ በኋላ የአገሩን ፀጥታና ዳር ድንበር ከማስከበር አልፎ በኮሪያና በኮንጎ ዓለም አቀፋዊ ግዳጁን በመወጣት ዝናን አትርፏል፡፡ ሕዝቡንም በሁለት ጊዜ ሽግግሮች በጥሩ ሥነ ምግባር ያላንዳች ግጭትና የመከፋፈል ስሜት ተረጋግቶና ተሳስቦ እንዲቆይ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱ አይዘነጋም፡፡

ትጥቅ የመፍታት አተካራና የመንግሥት ተገዳዳሪነት

ሐሙስ ጥቅምት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ባሰሙት ንግግር ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በፓርላማ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለተጠየቋቸው አሥር ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ካነሷቸው ነጥቦች አንዱ በአንድ አገር ውስጥ በቡድን የመታጠቅ መብት ያለው መንግሥት ብቻ ነው የሚለው ነበር፡፡