Skip to main content
x

በ33 ሚሊዮን ዶላር የብረት ፋብሪካ ተገንብቶ ተመረቀ

በደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች የተቋቋመው ኢኮስ የብረታ ብረት ማምረቻ ኃላፊነቱ የግል ማኅበር፣ በ33 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባው ፋብሪካ በይፋ ተመርቆ ተከፈተ፡፡ ኩባንያው በዱከም ከተማ ያስገነባውን ፋብሪካ ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲያስመርቅ፣ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ጨምሮ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢሕአዴግ ጉባዔ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን አስመልክቶ ያደረገው ግምገማና የትኩረት አቅጣጫዎች

ከመስከረም 23 እስከ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ የከተሙት አንድ ሺሕ የኢሕአዴግ 11ኛ ጉባዔ አባላት ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ባሻገር፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት የነበረውን የአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታና የመንግሥትን አፈጻጸም ገምግመዋል፡፡

የካናዳ ባለሙያዎች በአወዛጋቢው የለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ ላይ ጥናት ሊያካሂዱ ነው

በሻኪሶ ከተማ አካባቢ ነዋሪዎች በተነሳ ተቃውሞ ምክንያት ሥራውን እንዲያቋርጥ በተደረገው የሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ ንብረት በሆነው የለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ ላይ፣ የካናዳ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጥናት ሊያካሂዱ እንደሆነ ታወቀ፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር ጥረት ላይ ያለችው ኢትዮጵያ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዋ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪውን የ2010 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡ ሐሙስ ነሐሴ 10 ቀን 2010 ዓ.ም.

ለአዲስ አበባ ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የውጭ ምንዛሪ ተፈቀደ

የአዲስ አበባ ከተማን ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሻሻል ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ ለሆነው ኖርዝ አያት ፋንታ ጥልቅ ውኃ ፕሮጀክት የሚያስፈልጉ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም የውጭ ምንዛሪ እንዲፈቀድ በተደጋጋሚ ቢሞከርም ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አዲሱ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) እና አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ባካሄዱት ውይይት የውጭ ምንዛሪ መፈቀዱ ታወቀ፡፡

ባንኮች በሁለት ሳምንት ውስጥ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ መንዝረዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ የውጭ ገንዘብ በእጃቸው የሚገኝ ዜጎች ወደ ባንክ እንዲያስገቡ ማሳሰባቸው ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የግል ባንኮች ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በሁለት ሳምንት ውስጥ እንደመነዘሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጉዳይ

ባለፉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ያጋጠመው ከፍተኛ አመፅና የፖለቲካ አለመረጋጋት የሰዎችን ሕይወት ከመቅጠፍና ንብረት ከማውደም ባለፈ፣ በኢኮኖሚው ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይለካም እጅግ ከፍተኛ እንደነበረ መገመት አይከብድም፡፡