Skip to main content
x

አወዛጋቢው የረጲ ኃይል ማመንጫ ‹‹ቆሻሻ ከማቃጠል የዘለለ ሚና የለውም›› ሲሉ የውጭ ባለሙያ አጣጣሉ

ሥራ በጀመረ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንዲያቆም የተደረገውና ሦስት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ የፈሰሰበት የረጲ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ ቆሻሻ ከማቃጠል የዘለለ ሚና የለውም ሲሉ የዘርፉ የውጭ ባለሙያ አጣጣሉ፡፡

የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

በ2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ላለፉት ስድስት ዓመታት በእንግሊዝና በአይስላንድ ኩባንያ ካምብሪጅ ኢንዱስትሪስ ሲገነባ የቆየው የረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ግንባታው ተጠናቅቆ እሑድ ነሐሴ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ይመረቃል፡፡

በኦሮሚያ አርሶ አደሮች ተቃውሞ ሥራ ያቆመውን የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥራ ለማስጀመር ውይይት ሊካሄድ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ አርሶ አደሮች ተቃውሞ ሥራ ያቆመውን የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ ሥራ ለማስጀመር፣ ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናትና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ያቋረጠውን ውይይት ሊጀምር መሆኑ ታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የከተማውን ደረቅ ቆሻሻ በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድ የገነባው የሰንዳፋ ቆሻሻ ማስወገጃ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ምክንያት ሥራ በጀመረ በሰባት ወሩ ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ይታወሳል፡፡

የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ግንባታ መጠናቀቁ ተጠቆመ

በ120 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ከሦስት ዓመታት በፊት የተጀመረው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ፣ ግንባታው መጠናቀቁንና በሰኔ ወር አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ አስናቀ (ኢንጂነር) እንደተናገሩት፣ ረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ በ37 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ፕሮጀክት ነው፡፡

የቆሸሸች አበባ

ስለአዲስ አበባ ከተማ የዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫነቷ፣ የአፍሪካ መዲናነቷ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ መናኸሪያነቷ አይካድም፡፡ ይሁንና ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በተለየ መጎናፀፍ የቻለችውን ያህል፣ ስሟን በሚመጥን ቁመና ላይ ነች ወይ? ተንከባክበናታል ወይ? ሌሎችም በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ቢሯቸውን እዚህ እንዲከፍቱ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠርን ነው ወይ? ጠብቀናታል ወይ? የሚሉትን  ጥያቄዎች ብናነሳ የምናገኘው መልስ ልብ አይሞላም፡፡