Skip to main content
x

አክሱምን በምልዓት የሚታደጋት ማን ነው?

መሰንበቻውን አነጋጋሪ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ የአክሱም ሐውልቶችና ቅርሶች ለከፋ አደጋ መጋለጣቸው ነው፡፡ የሦስት ሺሕ ዓመታት ባለታሪኳ ጥንታዊቷ አክሱም የዛን ዐረፍተ ዘመን የሚያሳዩ፣ በመንበረ መንግሥትም ሆነ በመንበረ ክህነት የልዕልናዋ መገለጫ የሆኑ ግዙፉን ሐውልቶች፣ ቤተ መቅደሶች፣ የቤተ መንግሥት ፍራሾችን በዕቅፏ ይዛለች፡፡ ጽላተ ሙሴ የሚገኝበት የአራተኛው ምታመት ቅድስት ማርያም ጽዮን፣ የድንጊያ ዙፋኖች፣ የሐውልቶች ፓርክ፣ ድንጉር ቤተ መንግሥት፣ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡