Skip to main content
x

ክፍተት የታየበት የሐኪሞች የሥነ ምግባር ጥሰት ተጠያቂነት

በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አልፎ አልፎ ውስብስብ ስህተቶች ሲፈጸሙ ይስተዋላል፡፡ ከስህተቶቹም መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰው የታካሚው ኅልፈተ ሕይወት ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን ኅልፈቱ በበሽታው? ወይስ ከተደረገለት ሕክምና ጉድለት ነው? የሚለውን ለማወቅ ወይም ለመለየት የሚያስችል ምርመራ ማካሄድ ግድ ይላል፡፡ ይህ ዓይነቱንም ምርመራ የሚያካሂደው የተለያዩ የሕክምና ባለሙያዎች የተወከሉበት አካል ነው፡፡