Skip to main content
x

የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ በማኅበረ ሥላሴ ገዳም እስከሚቀበር በ‹‹ብሔራዊ ሙዚየም›› ይቆያል

ለዘጠኝ አሠርታት ግድም በመሳፍንት ተከፋፍላ የነበረችው ኢትዮጵያ አንድነቷን እውን ያደረጉት ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ናቸው፡፡ የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ በ19ኛው ዓመት የተጀመረውም አባ ታጠቅ በሚባለው የፈረስ ስማቸው በሚታወቁት በኚሁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ቴዎድሮስ ዘመን መሆኑ ይወሳል፡፡

‹‹ቦሬሳው ካሣ››

‹‹የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ፣ ልክ አድርገህ ተመልከት፡፡ ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት፡፡ ሁለተኛ ክብርህ ናት፡፡ ሦስተኛም ሚስትህ ናት፡፡ አራተኛም ልጅህ ናት፡፡ አምስተኛም መቃብርህ ናት፡፡ እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘመድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሳ፡፡››

የካራማራ - ጅግጅጋ ድል 41ኛ ዓመት

ዞሲማስ ሚካኤል ከሚኖርበት የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ 15 ቀበሌ 28 አዳራሽ የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም. በዕለተ እሑድ ምሽት ለወጣቶች የሚሰጠውን የፖለቲካ ንቃት (ትምህርት) እየተከታተለ ነበር፡፡ አዳራሹ ሙሉ ነው፡፡ ድንገት ውይይቱ ተቋረጠ፡፡ በቀበሌው ነዋሪ የሆነው ወጣቱ ተዋናይና የፕሮግራም አስተዋዋቂ በኋላ መቶ አለቃ፣ አሁን የማስታወቂያ ባለሙያ ብንያም በቀለ፣ ‹‹የምሥራች አለኝ›› እያለ ከመድረክ ላይ ወጣ፡፡

የሂሻም ኤል ግሩዥን የ22 ዓመት ክብረ ወሰኖች ያቆሙት ኢትዮጵያውያን

ታዋቂው ሞሮኮዊ አትሌት ሂሻም ኤል ግሩዥ በእነ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ወርቃማ የድል ዘመን ከሚጠቀሱ የአፍሪካ ፈርጦች አንዱ ነው፡፡ በመካከለኛ የሩጫ ርቀት መስክ በተለይም ከ1‚500 ሜትር እስከ 3.000 ሜትር ርቀት አልቀመስ ከማለቱም በላይ ከሁለት አሠርታት በላይ ሳይደፈሩ የቆዩ የዓለም ክብረ ወሰኖችን በማስመዝገብ ከቀዳሚዎቹ አትሌቶች ተካቶ ቆይቷል፡፡

በየካቲት 12 መነሻ

በኢትዮጵያ ታሪክ በተለይ ሉዓላዊነትን ለማስከበር፣ አገራዊ ልዕልናን ለማስቀጠል ከባዕዳን ወራሪዎች ጋር ታላቅ ተጋድሎ ከተደረገባቸው ወሮች አንዷና ባለ ፋናዋ የካቲት ነች፡፡ የሩቅ ዘመኑን ትተን ከቅርቡ 19ኛው ምዕት ዓመት ብንነሳ የጥቁሩን ዓለም ያገዘፈው የዓድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ በጣሊያን ላይ የተቀዳችው ድል ይጠቀሳል፡፡

የዓድዋ ድል ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች

‹‹እኛ ግን እንኳን ለእልፍና ለሁለት እልፍ ሰው የጣሊያን አገር ሰው ሁሉ ቢመጣ የጣሊያን ጥገኝነት ይቀበላሉ ብለህ አትጠራጠር!›› ይኼ ኃይለ ቃል የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ አውሮፓ ለነበረው ለሙሴ ኢልግ ነሐሴ 23 ቀን 1887 ዓ.ም. ከጻፉት ደብዳቤ ውስጥ የተገኘና ጳውሎስ ኞኞ አጤ ምኒልክ በሚል ርዕስ ካሳተሙት መጽሐፍ የተገኘ ነው፡፡

የሰማዕታቱ ቀን

ከሰማንያ ሁለት ዓመታት በፊት ፋሺስት ጣሊያን በአዲስ አበባ ከተማ የፈጃቸውና ሰማዕትነት የተቀበሉት ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም. በስድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት ተዘክሯል፡፡ የሰማዕታቱ ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራልም በጸሎተ ፍትሐት የታሰበው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (1923-1967) አማካይነት በ1934 ዓ.ም. በካቴድራሉ አፀድ ውስጥ በተተከለው የሰማዕታቱ አፅሞች ማረፊያ ነው፡፡

የባህል ልውውጡ የቶኪዮ የባህል ኦሊምፒያድ ይደርስ ይሆን?

የኢትዮጵያ የባህል ፖሊሲ የአገሪቱን ባህል ለተቀረው ዓለም በስፋት ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ በባህል እኩልነትና የጋራ ጠቀሜታ ላይ የተመሠረቱ ጠንካራ አገራዊ፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶች መፍጠር እንደሚገባ ያመለክታል፡፡