Skip to main content
x

‹‹ኑና የኢትዮጵያን ውበት ተመልከቱ!››

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቱሪስት ድርጅት ከ1950ዎቹ ጀምሮ ወርቃማው የአገራዊ ሀብት ማስተዋወቂያው ‹‹የአሥራ ሦስት ወራት ጸጋ›› (ሠርቲ መንዝስ ኦቭ ሰንሻይን) የኢትዮጵያ መለያ (መፈክር) ሆኖ ዘመናትን አስቆጥሯል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ‹‹ምድረ ቀደምት›› (ላንድ ኦቭ ኦሪጅን) የሚለው መለያው ተክቶታል፡፡

ዝገትን እንደ ቀለም

ሽበት የቀላቀለበት መወልወያ የመሰለ ጉድሩ (ድሬድ) ፀጉሩን እንደ ነገሩ አድርጎ ወደ ኋላ አስይዞታል፡፡ ከላይ የደረበው ቡራቡሬ የወታደር ዩኒፎርም መሳይ ጃኬቱ ላይ የለጣጠፋቸው ጨርቆች ጃኬቱን ይበልጥ አዥጎርጉሮታል፡፡ ለ39 ዓመቱ ቀራፂ ተስፋሁን ክብሩ ሁሉም ነገር በምክንያት የተፈጠረ የጥበብ እፍታ ነው፡፡ ሁሉም ዓይነት ፍጥረት፣ ክስተትና ሌሎችም ሥነ ምኅዳራዊ፣ ቁሳዊና መንፈሳዊ ክዋኔዎች ሁሉ የጥበብ ትሩፋቶችና በተዥጎረጎረው አለባበሱም የቀለማትን ውህደት፣ ተለያይነትና ሌሎችም ጥበባዊ ባህሪያትን ማሳየት ይፈልጋል፡፡

በቆራሊዮ አምሳል

‹‹አሮጌ ጫማ ብልቃጥ ጠርሙስ ቆርቆሮ ያለው›› የሚለውን ለየት ያለ ዘዬ ያለውን የቆራሊዮ ጥሪ ተከትለው ከበረንዳ ጫማ፣ ከመደርደሪያ ጠርሙስ፣ ከጓሮ መዘፍዘፊያና የብረት ቁርጥራጭ ይዘው የሮጡ ጥቂት አይደሉም፡፡ ቆራሊዮ የበርካቶች የልጅነት ትዝታም ጭምር ነው፡፡ የቅባት ጠርሙስ በ30 ሳንቲም ሸጠው ብስኩት ገዝተው የበሉ ብዙ ናቸው፡፡ አይጠቅሙም ተብለው የተጣሉ ቅራቅምቦዎች ሳይቀሩ ለቆራሊዮ ዋጋ አላቸው፡፡

ለ13 ዓመታት የአንበሳ አውቶቡስን አንበሳ የሣለችው  አርቲስት

‹‹ዘመን›› የተሰኘው የዓይናለም ገብረማርያም የሥዕል ዐውደ ርዕይ፣ የሠዓሊቷን የ40 ዓመታት ሥነ ጥበባዊ ጉዞ ያስቃኛል፡፡ በአዲስ አበባ ሙዚየም ከጥር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለ15 ቀናት ይታያል፡፡ ሠዓሊቷ እንደምትናገረው፣ በ1970ዎቹና 80ዎቹ በ90ዎቹም የሠራቻቸው ሥራዎች በምን ሒደት እንዳለፉ የምታሳይበት ዐውደ ርዕይ ነው፡፡ ‹‹የ40 ዓመታት ጉዞዬን ሕዝቡ እንዲያይ እፈልጋለሁ፡፡ በየወቅቱ ያለው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ማሳያም ነው፤›› ትላለች፡፡