Skip to main content
x

ዶ/ር መረራ ጉዲና ጨምሮ የ22 ተከሳሾች ክስ ተቋረጠ

በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው ጉዳያቸውን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በቀጠሮ በመከታተል ላይ የነበሩት ዶ/ር መረራ ጉዲና እና 22 ተከሳሾች ክሳቸው እንዲቋረጥ መወሰኑ ተረጋገጠ፡፡ በዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ፊርማ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የተላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ ዶ/ር መረራም ሆኑ ሌሎች በክስ ላይ የነበሩ ተከሳሾች ክሳቸው ተቋርጧል፡፡