Skip to main content
x

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተሾሙ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጀት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉሬቴዝ የድርጅቱ የኬንያ ቢሮ ዳይሬክተር ጄኔራል በመሆን ተሾሙ፡፡ የተመድ ዋና ጸሐፊ ቃል አቀባይ ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም.

ከ8.3 ሚሊዮን በላይ ወገኖች አስቸኳይ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመድ አስታወቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ማክሰኞ የካቲት 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ቅድመ ሪፖርት፣ በዚህ ዓመት ከ8.3 ሚሊዮን በላይ ወገኖች አስቸኳይ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል አለ፡፡

ከኢትዮጵያ በዘጠኝ ዓመታት 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሸሸ ሪፖርት ተደረገ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት  (ተመድ) ሥር የሚገኘው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው የአፍሪካ የጤና ክብካቤና የኢኮኖሚ ዕድገት ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ወደ ውጭ በሕገወጥ መንገድ እንደሸሸባት አስታውቆ፣ ይህ ገንዘብ ለጤናው ዘርፍ የምታውለውን 87 በመቶ በጀት እንደሚሸፍን አመለከተ፡፡

የኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ቆይታና ውጤቱ

ኢትዮጵያ የዛሬ ሁለት ዓመት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በመሆን የተመረጠችው ታኅሳስ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ነበር፡፡ በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት አባልነት ድምፅ ከሰጡ 190 አባላት አገሮች መካከል የ185 አገሮችን ድምፅ በማግኘት የተለዋጭ አባልነት መንበሩን ስትቆናጠጥ የነበረው ጥያቄ፣ ይህ አባልነት ለአገሪቱም ሆነ ለቆመችለት ዓላማ ምን ፋይዳ ይኖረዋል የሚል ነበር፡፡

‹‹ኢትዮጵያዊነትን ከሰላም ጋር አንድ ለማድረግ መሥራት አለብን›› ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ወ/ሮ ዘውዲቱ ምኒልክን ንግሥተ ነገሥታት፣ ራስ ተፈሪ መኮንን ደግሞ ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ በማድረግ መስከረም 17 ቀን 1909 ዓ.ም የዳግማዊ አፄ ምኒልክን ዙፋን ካረካከበው ታሪካዊ ክስተት ወዲህ፣ ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዚዳንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሹመዋል፡፡

ኢትዮጵያ በንግድ ጦርነት ጦስ ሊጠቁ ከሚችሉ ቀዳሚ አገሮች ተርታ ተመደበች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ (UNCATD) በዓለም ላይ እየታየ ያለውን የንግድና የታሪፍ ከለላ ዕርምጃ በተመለከተ በድረ ገጹ ባስነበበው ጽሑፍ፣ በወጪ ንግዳቸው ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ሊጋጥማቸው ይችላሉ ካላቸው ከ30 በላይ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያን በሦስተኛ ደረጃ አስቀምጧል፡፡

በደቡብና ኦሮሚያ አዋሳኝ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ደረሰ

በምዕራብ ጉጂና ጌዴኦ ዞኖች ተከስቶ በነበረው ግጭት የተፈናቃዮች ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መድረሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ ከቀናት በፊት ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርት እስካሁን ባለው አኃዝ መሠረት 527,263 ከምዕራብ ጉጂ ዞን ሲፈናቀሉ፣ 170 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ከጌዴኦ ዞን መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡

በውጭ ኢንቨስትመንት መዳረሻነት ኢትዮጵያ ደረጃዋን እንዳሻሻለች የተመድ ሪፖርት አመለከተ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ ማክሰኞ ማምሻውን ይፋ ባደረገው ዓመታዊ የኢንቨስመንት ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ያስመዘገበችውን ከፍተኛ ውጤት አስጠብቃለች፡፡

በተመድ የዓለም ኢንቨስትመንት ሪፖርት መሠረት፣ ባለፈው ዓመት ወደ አፍሪካ ከመጣው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ የኢትዮጵያ ድርሻ 3.2 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ይህም ከአንጎላ፣ ከግብፅ፣ ከናይጄሪያና ከጋና በመከተል አምስተኛ ደረጃ በመያዝ ከፍተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት መዳረሻ እንደነበረች ይታወሳል፡፡

ከ17 ሚሊዮን በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች በአንድ ዓመት ከአኅጉሪቱ እንደተሰደዱ ተመድ አመላከተ

በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ይፋ የሚደረገው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ ሪፖርት ዘንድሮ ትኩረቱን በስደተኞች ላይ ሲያደረግ፣ እ.ኤ.አ. በ2017 ብቻ ከአፍሪካ 17 ሚሊዮን ሰዎች ወደተለያዩ አገሮች መሰደዳቸውን እንዳመለካተ ተጠቁሟል፡፡

የድርቅና የብድር አቅርቦት ችግሮች ያቀዛቀዙት የኢትዮጵያና የምሥራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ዕድገት

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር የሚተዳደረው የአፍሪካ ኦኮኖሚክ ኮሚሽን በዚህ ዓመት ይፋ ያደረገውና የኢኮኖሚ ጉዳዮችን የቃኘው ሪፖርት፣ እንደ ኢትዮጵያ፣ ኬንያና  ታንዛኒያ ያሉ የምሥራቅ አፍሪካ ትልልቅ አገሮች የሚያስመዘግቡት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚጠበቀውን ያህል እንዳይሆን ካደረጉ ችግሮች ውስጥ ድርቅና የውጭ ብድር ዕጦት ትልቁን ድርሻ እየያዙ መምጣታቸውን አስፍሯል፡፡