Skip to main content
x

በገቢዎች ጽሕፈት ቤት ቃጠሎ ምክንያት የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ከምክትላቸው ጋር ከሥልጣን ተነሱ

ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት በእሳት ቃጠሎ ከወደመ በኋላ፣ ተገቢውን ዕርምጃ አልወሰዱም በሚል ምክንያት የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ አኬኔ ኦፓዳ እና ምክትላቸው አቶ ጀምስ ኬች ከሥልጣናቸው ተነሱ፡፡ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን) ለሳምንት ያህል ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቶ፣ ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ምክትላቸው ጥፋተኞች ናቸው በማለት ከሥልጣናቸው ማንሳቱ ታውቋል፡፡