Skip to main content
x

የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከሥራ መታገዳቸው ታወቀ

የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ከሥራ መታገዳቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡ እንደ ምንጮቻችን ገለጻ ከአሥር በላይ የሚሆኑ የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ከሐምሌ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ ታግደዋል፡፡

የኬንያ ትልልቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ዝግጅት ጀምረዋል

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር በኢትዮጵያ እንደሚተገብሩ ይፋ ካደረጋቸው ለውጦች መካከል የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉና በከፊል ወደ ግል እንደሚዛወሩ የሚለው፣ ከአገር ውስጥም ከውጭም ትልቅ ፍላጎት ፈጥሯል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ በቀድሞ የተቋሙ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተተኩ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዷለም አድማሴ (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸው የቀድሞ የተቋሙ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ተተክተዋል፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር የነበሩት አቶ ኢሳያስ ዳኘው ተነስተው፣ በምትካቸው ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር የነበሩት አቶ አማረ አሰፋ ተተክተዋል፡፡

የግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ጅምሮች

ሶፊያ የተሰኘችው ሰው መሰሏ ሮቦት በኢትዮጵያውያን የተጎበኘችበት የዘንድሮው የአይሲቲ ዓውደ ርዕይ ካስተናገዳቸው በርካታ ኩነቶች መካከል አንዱ የግብርናው ዘርፍ ላይ ሲካሄዱ የነበሩ አንዳንድ የቴክኖሎጂ ትግበራዎች የተቃኙበት መድረክ ይጠቀሳል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮምን አጠቃላይ የሀብት መጠን ለመለካት አራት የውጭ ኩባንያዎች ይወዳደራሉ

መንግሥት ሙሉ በሙሉና በከፊል ወደ ግል እንደሚያዛውራቸው ይፋ ካደረጋቸው የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም፣ በአሁኑ ወቅት ያሉት ቁሳዊና ሌሎችም ሀብቶቹ ተጠቃለው እንዲተመኑና አጠቃላይ ሀብቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ አራት የውጭ አማካሪ ኩባንያዎችን ለማነጋገር መዘጋጀቱ ታወቀ፡፡

መንግሥት የኢትዮ ቴሌኮምን አጠቃላይ የዋጋ ትመና ለመሥራት አራት ትልልቅ አማካሪዎች ሊያናግር ነው

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትልልቅ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ይዞታ በአክሲዮን ሽያጭ ለማስተላለፍ በወሰነው መሠረት፣ የኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ የዋጋ ተመን እንዲሠሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ አራቱ ትልልቅ አማካሪዎች በመባል የሚታወቁትን ድሎይት፣ ኬፒኤምጂ፣ ኧርነስት ኤንድ ያንግና ፒደብልዩሲ ከተባሉትን ድርጅቶ ውስጥ አንዱን ለመቅጠር ማሰቡ ታወቀ፡፡

የቴሌኮም ነገር ሁለት ወደፊት አንድ ወደ ኋላ

ኢትዮ ቴሌኮም ከሚተገብራቸው አሠራሮች ውስጥ ከውጭ የሚገቡ የእጅ ስልኮች በአገር ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል ነው፡፡ የተዘጉ ስልኮችን በመክፈት አገልግሎት ላይ እንዲውሉ እያደረገ ነው፡፡ እንዲህ ያለውን አገልግሎት በተለያዩ ቅርንጫፎቹ የሚሰጥ ሲሆን፣ ይህም በሕገ ወጥ መንገድ የሚገቡ የሞባይል ስልኮችን ለመቆጣጠርና የአገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታት ያለመ አሠራር ነው፡፡

ኢሕአዴግ ባድመ ለኤርትራ እንድትሰጥ የወሰነውን የአልጀርስ ስምምነት ሙሉ በሙሉ መቀበሉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማክሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፣ ባድመ ለኤርትራ እንድትሰጥ የወሰነው የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ እንደወሰነ አስታወቀ፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አመሻሸ ላይ ባወጣው መግለጫ ከ20 ዓመታት ውዝግብና እሰጥ አገባ በኋላ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የድንበር ማካለል ኮሚሽን የወሰነውንና በሁለቱ መንግሥታት በአልጀርስ የተፈረመውን ስምምነት እንደሚቀበል ይፋ ሲያደርግ ምክንያቱ ምን እንደሆነ አሥፍሯል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በዘጠኝ ወራት ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ካቀረባቸው አገልግሎቶችና የምርት አማራጮች የዕቅዱን 27.79 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስገባት እንደቻለ  አስታወቀ፡፡ ኩባንያው የዘጠኝ ወራት አፈጻጸሙን በማስመልከት ለሪፖርተር በላከው መግለጫ፣ 29.95 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ለማስገባት ቢያቅድም የዕቅዱን 93 በመቶ ያሳካ ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ገቢው የ15 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብሏል፡፡