Skip to main content
x

ኢትዮጵያና ሩዋንዳ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ የመጀመርያው የአገር መሪ በመሆን ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙትን የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜን፣ ዓርብ ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በታላቁ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ሐሙስ ዕለት ምሽት አዲስ አበባ ሲገቡ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ተቋም ተባለ

በየዓመቱ በዱባይ አዘጋጅነት በሚካሄደው ዓለም ዓቀፉ የኢንቨስትመንት ጉባዔ፣ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ውጤታማ አፈጻጸም ያሳዩ አገሮች ተወዳድረው በሚሸለሙበት መድረክ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ የዘንድሮውን ሽልማት ማሸነፍ ችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ዝምታዋን ናይጄሪያና ኡጋንዳ ሥጋታቸውን ያሳዩበት የአፍሪካ የነፃ ገበያ ስምምነት ዛሬ ይፈረማል  

የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አራት ዓመታት ውስጥ የጉምሩክ ታሪፏን ሙሉ በሙሉ ልታነሳ እንደምትችል ብቻም ሳይሆን፣ የአፍሪካ የነፃ ገበያ ስምምነትን ለመፈረም መዘግየቷን እንደማይቃወም ከወራት በፊት ለሪፖርተር አስታውቆ ነበር፡፡

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት ቁርጥ ያሉ ውሳኔዎች ያልተላለፉበት 30ኛው የመሪዎች ጉባዔ

30ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጥር 20 እና 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በአሁኑ የመሪዎች ጉባዔ የፀረ ሙስና ዘመቻ፣ የአፍሪካ ኅብረት ማሻሻያ፣ ነፃ የንግድ ቀጣና መመሥረት፣ የአፍሪካን የአየር ክልል ለአፍሪካ አየር መንገዶች ነፃ ማድረግና በአኅጉሪቱ በሚታዩ የፀጥታ ሥጋቶችና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ባለፈው እሑድና ሰኞ በተካሄደው 30ኛው የመሪዎች ጉባዔ የአርባ ዘጠኝ አገሮች መሪዎች ተገኝተው ነበር፡፡

የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ተቃውሞ ገጠመው

የአፍሪካን የአየር ትራንስፖርት አውታር ወደፊት እንደሚያራምድ የታመነበት የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ገበያ በክልከላ የተተበተበ በመሆኑ የአፍሪካ የአየር መንገዶች ዕድገት ፈታኝ እንዳደረገው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የገበያ ክልከላን በማስቀረት የአፍሪካ አየር መንገዶች አፍሪካ ውስጥ በነፃነት ከአገር አገር እንዲበሩ የሚያስችል የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ፣ ጥር 20 እና 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተካሄደው 30ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ በይፋ አውጇል፡፡ ሰኞ ጥር 21 ቀን በተካሄደው የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ መመሥረቱን ያወጁት አዲሱ የኅብረቱ ሊቀመንበር የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ናቸው፡፡ ፖል ካጋሜ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ ለአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዕድገት ትልቅ ዕርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡